‹‹ሰልፍ ወጣን፤ ጥይት መተኮስ ጀመረ›› የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

Source: https://mereja.com/amharic/v2/117285

አብመድ ያነጋገራቸው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ ችግሩ የተፈጠረው ለአንድ ሳምንት ያክል የንጹሕ መጠጥ ውኃ ባለማግኘታቸዉና ዩኒቨርሲቲው አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ የሚመለከተውን አካል ለመጠየቅ ሰልፍ በወጡበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሰልፍ ወጣን፤ ጥይት መተኮስ ጀመረ›› ብለዋል፡፡
‹‹እኛ ሰልፍ እንደወጣን ውኃው ተለቀቀ፤ ይህ ማለት ችግሩ ከአቅም በላይ ሁኖ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ባለመስጠቱ የተፈጠረ ችግር ነበር ማለት ነው›› ብለዋል ተማሪዎቹ፡፡
‹‹ያች ቅፅበት ቀኝ እግሬን አሳጥታኛለች፤ … ከበፊቱ ቢሻለኝም… ያመኛል›› በህክምና ላይ ያለው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
‹‹ታካሚው በጥይት ነው የተመታው የሚባለው ነገር ትክክል አይደለም፡፡›› የባሕር ዳር ጥበበ ግዮን ሪፈራል ሆስፒታል
ሰሞኑን በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ያለመረጋጋት ጉዳት ደርሶበት በባሕር ዳር ጥበበ ጊዮን ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተለ ያለው የ3ኛ ዓመት ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ታደለ በዛ ጋር አብመድ ቆይታ አድርጓል፡፡

‹‹ራሴን ያገኘሁት ሆስፒታል ውስጥ ተኝቼ ነው፡፡ የሆነው ነገር ሁሉ ማስታወስ አልቻልኩም፡፡ አሁን ላይ ሆኜ የማስታውሰው ነገር ቢኖር ያለፈው እሑድ ለሳምንት ያህል በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የውኃ እጥረት መፈጠሩን ተከትሎ ሰልፍ ተደርጎ ነበር፤ ሰልፉን ለመበተን የገቡ የፌዴራል ፖሊሶች ደግሞ በየብሎኩ ሲያሯሩጡን ነበር፤ እስከምሮጥ ድረስ፤ አስታውሳለሁ ከዚያ በኋላ ግን ራሴን ያገኘሁት ሆስፒታል ውስጥ ነው፡፡ ያች ቅፅበት ቀኝ እግሬን አሳጥታኛለች፤ …ከበፊቱ ቢሻለኝም… ያመኛል›› ብሏል ተማሪ ታደለ በዛ፡፡
አብመድ ስለጉዳቱ መንስኤ ያነጋገረው ተማሪ ታደለ ‹‹ጉዳቱ በምን እንደደረሰብኝ አላውቅም›› ብሏል፡፡
የጥበበ ግዮን ሪፈራል ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ድሕረ ምረቃ ሐኪም ዶክተር አደራው ጌቴ ‹‹ተማሪ ታደለ ከ13 ሰዓታት በኋላ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.