ሰማይ ተቀደደ ቢሉት ሽማግሌ ይሰፋዋል ይላሉ አበው – አማኑኤል ታደሰ (ከድሬዳዋ)

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/106717

በኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ይዘን የቆየነው ማህበራዊ መሠረታችን አንዱ ለሀገር ሽማግሌዎች የምንሰጠው ስፍራ ነው።የሀገሬው ህዝብ ከትንሹ የግለሰብ እና የቤተሰብ ግጭት ጀምሮ እስከ ትላልቅ ህብተረሰባዊ ጉዳዮች ድረስ በሽምግልና የመፍታት ባህልን ያዳበረ ትልቅ ህዝብ ነው። የተለያየ ባህል፣ እምነት፣ ቋንቋ፣ ሀይማኖትና የአኗኗር ዘይቤዎች ልዩነት ቢኖረውም እንኳን ይህ ህዝብ በመሀከሉ ለሚፈጠሩ ችግሮችና ግጭቶች ሽምግልናን እሴቱ አድርጎ ለዘመናት ኖሯል ዛሬም እየኖረ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች የተጣላን ያስታርቃሉ፣ የተጣመመን በጥበበብ ያቃናሉ፣ የጎደለን አለስስት ይሞላሉ:: በሰዎች እና በህዝቦች መሀከል የተፈጠረን ቅራኔ ለመፍታትና ለማጥበብ ከሚደረግ ጥረት ባሻገር ሽምግልናን በአንድ ሀገር ውስጥ በሚኖሩ የአካባቢ ነገስታት መሀከል የተፈጠረን የጥቅምና የስልጣን ሽኩቻን ለማርገብ የምንጠቀምበት መሳሪያም ሆኖ አገልግሏል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገር ሽማግሌዎች ያለው ቦታ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.