ሰሜን ኮሪያ አዲስ በቴክኖሎጂ የበለጸገ መሳሪያ መሞከሯ ተሰማ

Source: https://fanabc.com/2018/11/%E1%88%B0%E1%88%9C%E1%8A%95-%E1%8A%AE%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%89%A0%E1%89%B4%E1%8A%AD%E1%8A%96%E1%88%8E%E1%8C%82-%E1%8B%A8%E1%89%A0%E1%88%88%E1%8C%B8%E1%8C%88-%E1%88%98/

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2011(ኤፍቢሲ) የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጁንግ ኡን በዓይነቱ የተለየና በቴክኖሎጂ የበለጸገ አዲስ መሳሪያ መሞከራቸው ተሰማ፡፡

ሆኖም የመሳሪያው ዓይነት በቴክኖሎጂ ከመበልጸጉ ውጭ በግልጽ ምን ዓይነት መሳሪያ እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሙከራው የተካሄደው በሀገሪቱ ብሄራዊ መከላከያ ሳይንስ ውስጥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አልጀዚራ የሀገሪቱን መገናኛ ብዙሃን ጠቅሶ እንደዘገበው፥ ኪም ከመሳሪያው ሙከራ በኋላ በመከላከያውና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚገኙ ተመራማሪዎች የሀገራቸውን የመከላከል አቅም ማጎልበት በመቻላቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ሙከራው ሰሞኑን ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ አነስተኛ የሆነ የጦር ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ የመጣ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በኒውክሌር ጉዳይ ላይ በሲንጋፖር ከተወያዩ በኋላ እንዲህ ዓይነት የመሳሪያ ሙከራ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፦አልጀዚራ

በአብርሃም ፈቀደ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.