ሰበር መረጃ ======== በምስራቅ ወለጋ ጃርቲ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት… 6/2013 ዓ.ም ባህርዳር…

ሰበር መረጃ ======== በምስራቅ ወለጋ ጃርቲ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት… 6/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// ነዋሪዎቹ ጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ቤት የማቃጠልና ተኩስ የመክፈት ዘመቻ እንደተካሄደባቸው ገልፀው ህይወታቸውን ለማዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በጫካ ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ‹‹ከወረዳው የተላኩ የክልሉ ልዩ ሀይሎች ሊታደጉን አልቻሉም፤በዚህ ሰዓት ከባድ አደጋ ውስጥ ነን፤ መንግስት ሊደርስልን ይገባል ብለዋል፡፡ ‹‹ከዚህ በፊትም ሰዎች ለገበያ በወጡበት ተገድለው እየቀሩ ነገሩ በዝምታ እየታለፈ ለችግር ተዳርገናል ›› ብለዋል፡፡ በወረዳው የሚገኙ ከ200 በላይ አማራዎች ቤትና ንብረታቸው እንደተቃጠለ እና እንስሳቶቻቸውም እንደተዘረፉ ገልፀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ጥቅምት 4/2013 በተከፈተባቸው ጥቃት 9 ሰዎች አድራሻቸው እንደጠፋ እና እስካሁን ያሉበት እንደማይታወቅ ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ መረጃውን እስካጠናቀርንበት ጥቅምት 6/2013 ዓ.ም ነዋሪዎቹ በአደጋ ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀው‹‹አሁን ቤታችን እና ንብረታችን ወድሟል ህይወታችን ያለው ጫካ ውስጥ ነው ታደጉን ሲሉ ተማፅነዋል፡፡ ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች በምስራቅ ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ዞን ጃርቲ ወረዳ በጫካ ውስጥ ከሚገኙ አማሮች ጋር ያደረግነውን የስልክ ቆይታ በአሻራ ሚዲያ የዩቲዩብ ቻናል ይከታተሉ !! https://youtu.be/c29BsQG0thg

Source: Link to the Post

Leave a Reply