ሰበር ዜና፣ ህወሃት ኃይለማርያም ደሳለኝን ከሥልጣን እንዳነሳ አስታወቀ

Source: http://www.mereja.com/amharic/565026

ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ ያነሳው የአገዛዝ ሥርዓት ለውጥ ጥያቄ እጅግ ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ በመሆኑና አገዛዙ ለህዝብ ጥያቄ አግባብ ያለው መልስ ለመስጠት ባለመቻሉና እየተሽመደመድና በመሄድ ላይ በመሆኑ ለይስሙላ የተቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣናቸው እንደሚለቁ ታውቋል። የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔ አገዛዝን አሽቀንጥሮ ለመጣል የሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፎች፣የስራ ማቆምና ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ምክንያት በመናወጥና በመንገዳገድ ላይ ያለው አገዛዝ በትዕዛዝ መመሪያ እየተቀበሉ የሚያገለግሉትን ኃይለማርያም ደሳለኝን አንስቶ በምትካቸው በቀጥታ በህወሃት አባል ለመተካት ውስጥ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው እንቅስቃሴ አሁን በይፋ ወጥቷል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በየካቲቲ 1966 ዓ.ም. የአክሊሉ ሐብቴ ጠቅላይ ሚኒስቴርነትን በእንዳልካቸው መኮንን ሲተካ “ጉልቻ ቢለወጥ ወጥ አያጣፍጥም” በማለት አገዛዙን ገርስሶ እንደጣለው ሁሉ የወያኔ አገዛዝ ተገርስሶ ካልወደቀ በአገሪቱ ውስጥ ሰላም፣ ዲሞክራሲና እድገት እንደማይመጣ ይታወቃል። ከኃይለማርያም ደሳለኝ መነሳት ማወቅ የሚቻለው ህወሃት የተነሳበትን ተቃውሞ ከአሁኑ በከፋ ሁኔታ በጉልበት ለመጨፍለቅ የከሸፈ ሙከራውን እንደሚቀጥለበት ለመረዳት ይቻላል።

Share this post

2 thoughts on “ሰበር ዜና፣ ህወሃት ኃይለማርያም ደሳለኝን ከሥልጣን እንዳነሳ አስታወቀ

  1. This is stupid article – article based on guess work. The Parliament is the one that certifies the PM. It is either demeke or lemma or Gudu. The is the logical conclusion. Parliament probably removed hailemariam.

    Reply

Post Comment