ሰበር ዜና በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በገደለው ሰው ቤት ለእዝን በተቀመጡ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት መበተኑን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

ሰበር ዜና በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በገደለው ሰው ቤት ለእዝን በተቀመጡ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት መበተኑን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

ሰበር ዜና በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በገደለው ሰው ቤት ለእዝን በተቀመጡ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት መበተኑን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ሲደን ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ የኔአለም አየለ ጥቅምት 5 ለ6 ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ቦንብ በመወርወርና ጥይት በመተኮስ መግደሉና ልጁንም በከፍተኛ ማቁሰሉን መዘገባችን ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሀዘንተኞች የአቶ የኔአለምን አስከሬን ወደ አሙሩ ወረዳ ሲደን ቀበሌ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመውሰድ ስርዓተ ቀብሩን መፈፀማቸው ተገልጧል። ይሁን እንጅ ስርዓተ ቀብሩን ፈፅመው የሟች ቤተሰቦችን እያፅናኑ ባሉ ለቀስተኞች ላይነከቀኑ 10 ሰዓት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈት የበተኑት መሆናቸውን ሸሽተው ወደ ጫካ የገቡ ነዋሪዎች ተናግረዋል። መከላከያም ሆነ ሌላ የፀጥታ አካል የለም ሲሉ ነው የድረሱልን ጥሪ ያስተላለፉት። የቀበሌው የፀጥታ አካላትም ህዝቡን ከመከላከል ይልቅ ሸሽተው መደበቃቸውን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ኦነግ ሸኔ ገድሎ ሀዘን ላይ እንዳንቀመጥ ከለከለን ሲሉ አማረዋል። የአሙሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪም ጠዋትም ሆነ ከሰዓትም ስንደውልላቸውና በፁሁፍ መልዕክት ብናደርሳቸውም ስብሰባ ላይ ነኝ በማለት ለማናገር አልፈቀዱም። በአንጻሩ የሲደን በርከሊ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረጀ ቶሌራ በበኩላቸው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው ከገቡ 2 ሳምንት እንደሆናቸው በመግለፅ ከቀበሌው አቅም በላይ መሆናቸውን ለአሙሩ ወረዳ ሪፖርት አድርጌያለሁ ብለዋል። የቀበሌው ምሊሻዎችም ወደ ወረዳ ተጠርተው ስልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን አቶ ደረጀ ቢናገሩም ነዋሪዎቹ ግን ፈርተው እንደሸሹ ነው የገለፁት። የሚመለከተው የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስት እንዲደርስላቸው ነዋሪዎችበጥሪነያቀረቡት። በኦነግ ሸኔ ጦር የተገደለው አቶ የኔአለም አየለም ሆነ አሁን ተኩስ የተከፈተባቸው ሀዘንተኞች ሁሉም የአማራ ተወላጆች መሆናቸውን ለማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከቀበሌ መዋቅሩም አንድም ሰው ለቅሶ ላይ አለመገኘቱ ተነግሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply