ሰበር ዜና – የአሜሪካ ምክር ቤት ኤች አር 128ን አፀደቀ

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/43732

አባይ ሚዲያ ዜና
ሱራፌል አስራት

የአሜሪካ የሕግ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እንዲከበርና የዲሞክራሲ ምህዳሩ እንዲሰፋ የሚጠይቀውን ኤች አር 128 ተብሎ የሚታወቀውን ህገረቂቅ  በአብላጫ ድምጽ ድጋፍ በመስጠት አጽድቆታል። 

ይህ ህገ ደንብ ወደ ድምጽ መስጠት ሂደት ከመምጣቱ በፊት የህግ ምክር ቤቱ የተባበሩት መንግስታት የምርመራ ቡድን በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመ ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲያካሂድ የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃድ እንዲሰጥ መጠየቁ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጥሰት አጣሪ ኮሚሽንን በኢትዮጵያ ገብቶ ምርመራ እንዲያካሂድ ፍቃድ እንዲሰጥ እና ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ቀነ ገደብ ተስጦት በቀነ ገደቡ ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል።

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በተሰጠው ቀነ ገደብ ምላሽ ለመስጠት ባለመቻሉ ይህ ኤች አር 128 ተብሎ የሚታወቀውን ህገረቂቅ በቀትታ ለውሳኔ ድምጽ እንዲቀርብ ተደርጓል።

በተለያዩ የውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶች፣ የሲቪክ ማሀበራት እንዲሁም አለማቀፍ የሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ይህን ኤች አር 128 ተብሎ የሚታወቀውን ህገረቂቅ እንዲያልፍ የበኩላቸውን አስተዋፆ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለውን የመብት ረገጣ እና ግድያ እንዲቆም እንዲሁም ንጽኋን ኢትዮጵያውያንን ያስገደሉ፣ ያሳሰሩ እና ያሰቃዩ የአገዛዙ ባለስልጣናት ወደ ፍርድ እንዲቀረቡ የሚያደርገውን ይህን ኤች አር 128 ተብሎ የሚታወቀውን ህገረቂቅ ድጋፍ እንዲያገኝ ኢትዮጵያውያን የኢሜል፣ የቲዊተር እንዲሁም የስልክ ዘመቻ በማድረግ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላትን ሲጠይቁ ሰንብተዋል።

ኤች አር 128 ህገረቂቅ ከሰባዊ መብት አከባበር በተጨማሪ የሚከተሉት እንዲተገበሩ ይጠይቃል።

  1. የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች ከመጠን ያለፈ ሀይል እንዳይጠቀሙ
  2. በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተካሄደው ግድያና ድብደባ እንዲጣራ
  3. ሁሉም የፖለቲካ እሰረኞች፥ጋዜጠኞች፥ አክቲቪስቶችና ያላግባብ የታሰሩ ከእስር እንዲፈቱ
  4. የሚዲያ ነፃነትና ሰላማዊ ተቃውሞ እንዲፈቀድ
  5. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባዊ ጥሰት ምርመራ እንዲአደርግ እንዲፈቀድ
  6. ሰላማዊ ኢትዮጵያዊያኖችን የገደሉና ቶርቸር ያደረጉ ለፍርድ እንዲቀርቡ
  7. በቂልንጦ፥በኢሬቻበአልና በሶማሊያ ክልል የተፈፀመው ግድያ ምርመራ እንዲካሄድ
  8. የፀረ ቴረሪዝም ህጉ እንዲሻር 
  9. የአስቸኮይ ግዜ አዋጁ እንዲነሳ የሚሉ ይገኙበታል

Share this post

One thought on “ሰበር ዜና – የአሜሪካ ምክር ቤት ኤች አር 128ን አፀደቀ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.