ሰው መሆን ይበቃል (ዘ-ጌርሣም)

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/107614

ህይወት ተገብሮ ከአገሩ ተባርሮ የአገር ሀብት ጨምሮ በግፍ ተመዝብሮ ለስደት ተዳርጎ በአራዊት ተበልቶ እንደ እንስሳ ታርዶ ሳምባ ኩላሊቱ ሆድ እቃው ተሽጦ ባሀር ውስጥ ሰጥሞ ግፍን አጣጥሞ በጉልበታም ዱላ አከላቱን አጥቶ አንገቱ ተቀልቶ የተገኘውን ለውጥ አብሮ ለመደገፍ ሰው መሆን ይበቃል አለያም ዞር ማለት ከመሆን አንቅፋት ሌሎች እንዲጓዙ በአንድ ላይ የቆሙት ዶክተር ፕሮፌሰር ጀኔራል ኢንጅኔር ሌላም ሌላም መባል ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እራስን ማታለል ትርጉምም የላቸው ቅንነት ያዘለ ዕውነት ከሌላቸው ቅን መሆን ይበልጣል እራስን ከመውቀስ ከፀፀት ያድናል አብሮ ለመሻገር ግቡ ላይ ለመድረስ የጠፋውን ጊዜ በልማት ነው መካስ የተገኘውን ለውጥ አብሮ ለመደገፍ እጅና ጓንት ሆኖ ውጤቱን ለማግዘፍ ሰው መሆን ይበቃል አለያም ዞር ማለት

The post ሰው መሆን ይበቃል (ዘ-ጌርሣም) appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.