ሱዳናውያኑ ለመነጋገር ተስማሙ

Source: https://amharic.voanews.com/a/sudan-talk-6-12-2019/4956511.html
https://gdb.voanews.com/9467cacf-c7fa-4ccb-8780-0fd90a61512b_tv_w800_h450.jpg

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና ተቃዋሚዎቹ ተቋርጦ የነበረውን ውይይት ለማስቀጠል በሚያስችሉ አምስት ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
ወገኖቹ ለመነጋገር የተስማሙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የጀመሩትን የማግባባት ሙከራ ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።
የስምምነቱን ጉዳይ ይፋ ያደረጉት በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደርና የሱዳን ዕርቅ ጉዳይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መሃመድ ድሪር ናቸው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.