ሱዳን እስረኛ እያስፈቱ እኛ በማናውቀው ወንጀል ማሰረ አይምሮዊ ቶርቸር ለማድረግ ነው – ስንታየሁ ቸኮል

Source: https://mereja.com/amharic/v2/139413

” የአዲስ አበባ ወጣቶች ክስ ሳይመሰረትባቸው 1 ዓመት ” ( በይድነቃቸው ከበደ)
ዛሬም እንደ-ወትሮው በእስር ቤት የሚገኙት ወንድሞቻችን እንዴት ናችሁ ?! ለማለት ፤ እኔ ፣ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ፣ ናትናኤል የአለምዘውድ እና ጌታነህ ባልቻ አንድ ላይ ሆነን ፤ ጠዋት አረፋፈዱ-ላይ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (3ኛ ፖሊስ ጣቢያ) ተገኝተን ነበር ።
Image may contain: 6 people, including Elias Gebru Godana, people smiling, beard
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፣ ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ ፣ መርከቡ ሀይሌ ፣ ስንታየሁ ቸኮል ፣ ሲሳይ አልታሰብ ፣ ክርስትያን ታደለ ፣ ምስጋናው ጌታቸው ፣ አዳም ውጅራ እና ሌሎች አብሯቸው የታሰሩ ወንድሞቻችን አግኝተናቸዋል። ሁሉም ለጤናቸው ደህና ናቸው ፤ በሁሉም ፊት ላይ የሚንጸባረቀው “መንግስት” ከወነጀላቸው ድርጊት ከቶውንም እንደሌሉበት እና በራስህ የመተማመን መንፈሳቸው በእጅጉ ሃይሎ ይታይባቸዋል።

በእኛ በኩል ለሁሉም ያቀረብንላቸው ጥያቄ ፤ ከሰሞኑ ምን የተለይ አዲስ ነገር በእስር ቤት ውስጥ አለ ?! በማለት ነበር ፤ በእነሱ በኩል ከበፊቱ ብዙም የተለየ ነገር እንደሌለ ከገለጹልን በኋላ ፤ እኛን መልሰው የጠየቁን “ውጪ ምን አዲስ ነገር ?! ” አለ በማለት ነበር ፤ ከነገርናቸው መካከል ” ዶ/ር ዐብይ ከሱዳን ከ100 በላይ እስረኛ አስፈትተው ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸውን ” ለሁሉም አግራሞት’ን የፈጠረ ነበር ።
ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ እንዲህ በማለት ሃሳብን አጋርቶናል ፦ ” በሰው ሃገር ያሉ ወገኖቻችን መፈታታቸው ደስ ይላል ፤ ነገር ግን በማናውቀው ወንጀል ተፈርጀን በሃገር ቤት እየታሰርን አሁን ደግሞ የምንሰማው ነገር ግራ የሚያጋባ ነው።

Share this post

One thought on “ሱዳን እስረኛ እያስፈቱ እኛ በማናውቀው ወንጀል ማሰረ አይምሮዊ ቶርቸር ለማድረግ ነው – ስንታየሁ ቸኮል

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.