ሲዳማ : ኢሕአዴግ ነሳ ፤ ኢሕአዴግ ሰጠ ፤ የኢሕአዴግ ስም የተባረከ ይሁን !

Source: https://mereja.com/amharic/v2/173610

ኢሕአዴግ ነሳ ፤ ኢሕአዴግ ሰጠ ፤ የኢሕአዴግ ስም የተባረከ ይሁን ! (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የሲዳማ ክልልነት እንደ አዲስ ነገር ሲራገብ ማየት ይገርማል። በተለይ የኦሮሞ ጽንፈኞችና የሕወሓት ካድሬዎች ወንጀላቸውን ለመደበቅ ይመስል ግንባር ቀደም አጨብጫቢዎች ሆነዋል።ታሪክን ለምናውቅ ክልልነት ለሲዳማ ሲያንሰው ነው። ከክልልነት በላይም ጠቅላይ ግዛት የነበረ ነው። ትላንት መብቱን የገፈፉት አካላት ዛሬ ላይ ዋና የደስታ አራጋቢ ሆነው ማየት ግርምትን ይፈጥራል።
ሲዳማ ሰፊ ክፍለ ሐገር ነበር ፤ ኢሕአዴግ መጣና ዞን አደረገው ፤ ቆራርሶም ለኦሮሚያ ክልል ሰጠው ፤ ከሻሸመኔ እስከ ዋደራ ሲዳማ በዙሪያው ተቆራርሶ በመለስ ዜናዊ ቡራኬ ለኦሮሚያ ክልልነት ተሰጠ። ሕወሓቶች ላለፉት ሐያ አመታት የሲዳማን ክልልነት ጥያቄ አፍነው ዛሬ ከአራት ኪሎ ከተባረሩ በኋላ ሲዳማ ክልል ሲሆን ያለነሱ ቀዋጭ ጠፋ። ሕወሓት በስልጣን ዘመኑ ስለክልልነት ሲነሳ የሲዳማን ሕዝብ እኮ ሲገርፍና ሲያሳድድ ነበር።
የኦሮሞ ጽንፈኞችም ቢሆኑ የሲዳማን ሕዝብ ለራሳቸው የነገ ፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ለማድረግ ፍላጎት ስላደረባቸው እያጨበጨቡ ነው። አልገባቸውም እንጂ ነገ ላይ የወሰን ጥያቄዎች ለከፍተኛ ደም መፋሰስ ይዳርጋሉ። የኦሮሚያ ክልል የመጀመሪያው አጨብጫቢ ቢሆንም ነገ ለሚነሳው ችግር ግን መልስ ለመስጠት እንደማይችል ያሳብቅበታል። ፖለቲካው በደንብ ይታወቃል ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች እያጨበጨቡ ያሉት ለነገ የሲዳማ ጥያቄዎች እንዳይነሱ ቀብድ መሆኑ ነው። በሲዳማና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ሰፊና የማይበርድ የወሰን ግጭቶች መነሳታቸው ውሎ አድሮ እናየዋለን።መንግስት ባልተጠና ፖሊሲ ወደ ፖለቲካ ኪሳራ ሲገባ በተደጋጋሚ እየተመለከትን ነው።
ሲዳማዎች የመብትና የወሰን ጥያቄ እንዳያነሱ ከፍተኛ የሆነ ብጥብጥና ግጭት በ አዲሱ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.