“ሴት ተማሪዎችን ባጠቃላይ ተመርመሩ ማለት መፈረጅ ነው” የሕግ ባለሙያ ወ/ሮ ሰብለ አሰፋ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/168444

BBC Amharic : ትላንት በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ፤ ሴት ተማሪዎች በመንግሥት ሆስፒታል የእርግዝና ምርመራ አድርገው በ48 ሰዓት ውስጥ ለፕሮክተራቸው (ለተቆጣጣሪዎች) እንዲያስገቡ የሚያሳስብ ማስታወቂያ መውጣቱ በርካቶችን አነጋግሯል።
ዩኒቨርሲቲው “ማስታወቂያው የወጣው በስህተት ነው” ሲል ማስተባበያ ቢያወጣም፤ ማስታወቂያው ለምን እና እንዴት ወጣ? ተማሪዎች እንዲመረመሩ ማስገደድ ሕጋዊ አግባብ አለው? በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በተደጋጋሚ ስለመውለዳቸው እና ህጻናት ተጥለው ስለመገኘታቸው የሚናፈሰው እውነት ነው? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች እየተሰነዘሩ ነው።
Image may contain: text
ማስታወቂያው የወጣው በተማሪዎች ኅብረት እንደሆነ የሚገልጸው የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዘዳንት ዳንኤል ጌታቸው፤ “ጠዋት ላይ [ሕዳር 28 ቀን 2012 ዓ. ም.] ውይይት ሳይኖር [በተማሪዎች ኅብረትና በዩኒቨርስቲው መካከል] በስሜታዊነት የተደረገ ነው፤ ስህተት መሆኑን አምነን ይቅርታ ጠይቀናል” ሲል ተናግሯል።
በእለቱ ጠዋት ልጅ ወልዳ መንገድ ዳር ጥላ የሄደች ተማሪ እንደነበረች የሚናገረው ዳንኤል፤ ክስተቱ ስሜታዊ እንዳደረጋቸው ገልጾ፤ ይህን ተከትሎ ማስታወቂያው የወጣው “ነገሩ ስላሳሳበን ነው” ይላል።
የተባለው ችግር በዩኒቨርስቲው አለ ቢባል እንኳን፤ የእርግዝና ምርመራ ይደረግ ብሎ ማስገደድ እንዴት መፍትሔ ይሆናል? ብለን ላቀረብንለት ጥያቄ፤ “ሌሎች ሴቶች ላይ እንዳይከሰት አስበን ነው፤ ባለማስተዋል የተደረገ ነው” ሲል መልሷል።
በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በተደጋጋሚ ይወልዳሉ? ህጻናት ተጥለው ስለመገኘታቸው የሚናፈሰው ወሬስ እውነት ነው? ብለን ጥያቄ ያቀረብንላቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ት መቅደስ ካሳሁን “ምን ያህል አለ? እስከዛሬ ምን ተሠራ? የሚለው መረጃ ተሰብስቦ እየተሠራ ነው። ሠርተን ይፋ እናደርጋለን” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
የተማሪዎች ኅብረት፣ የተማሪዎች ዲን እና ፕሮክተሮች፤ ዩኒቨርስቲው ላይ እውን ይሄ ነገር ይደጋገማል ወይ?

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.