ስልጤ ዞን ክልል እንዲሆን መጠየቁ ተሰማ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/186260

የስልጤን ህዝብ በክልል የማደራጀት ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራበት የዞኑ ነዋሪዎች የሠላም ሚኒስትሯን ጠየቁ። ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በዛሬው ዕለት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከወከሉት የስልጤ ዞን ህዝብ ጋር በወራቤ ከተማ ተገናኝተው መክረዋል።

በዚሁ ወቅት ለወ/ሮ ሙፈሪያት ህዝቡ ካቀረባቸው ጥያቄዎች መካከል የስልጤ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ገኝበታል።ከህዝቡ ለተነሳው ጥያቄ መልስ የሰጡት ሚኒስትሯ “የስልጤ ህዝብ በሌሎች ግፊት ምንም የሚያደርገው ነገር የለም፤ የትኛውንም መዋቅር ጥቅምና ጉዳቱን አመዛዝኖ ለመንግስት ማቅረብ ባለበት ጊዜ አቅርቦ ያስወስናል“ ብለዋል።
የቀድሞው ደኢህዴን ሊቀመንበር እና የአሁኑ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የስልጤን ህዝብ በክልል የማደራጀት ጥያቄን ጨምሮ ህዝቡ በተለያዩ ዘርፎች የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ህዝቡና አመራሩ ከምን ጊዜውም በተሻለ ቅንጅት እንዲሰራ ማሳሰብያ መስጠታቸውን ከስልጤ ዞን ህዝብ ግንኙነት ዩኒት ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።የስልጤ ዞን በደቡብ ከዚህን ቀደም በክልል የመደራጀት ጥያቄዎችን በምክር ቤታቸው ተቀብለው ካላጸደቁት ዞኖች መካከል መሆኑ ይታወሳል።
ስልጤ ዞን ህዝብ ግንኙነት ዩኒት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.