ስኳር ኮርፖሬሽን ከውጭ ገዝቶ ካስመጣው 2 መርከብ ስኳር ውስጥ 3 ሺህ 777 ኩንታሉ “የገባበት ጠፋ”!!

Source: http://welkait.com/?p=11213

የስኳሩ ጉዳይ…

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በመተሃራ ተበላሽቷል ተብሎ ስለተቀበረው ስኳር ማስረጃ አላገኘሁም አለ…

ስኳር ኮርፖሬሽን በውጭ ምንዛሬ ገዝቶ ወደ ሐገር ካስገበው 2 መርከብ ስኳር 3 ሺህ 777 ኩንታሉን ተበላሽቷል ብሎ ቀብሮታል ተብሏል፡፡ የዓይን እማኞች ጭምር አሉኝ ቢልም ስለመቅበሩ ግን ማስረጃ አላቀረበም፡፡ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርበው የተጠየቁት የሥራ ሃላፊዎቹ በጊዜው ስኳሩን የቀበርነው ውጭ ሐገር ድረስ ልከን መበላሸቱን እና ለምግብነት እንደማይውል ካረጋገጥን በኋላ ነው ብለዋል፡፡ ስኳሩ ብልሽት ያጋጠመው ከአቅራቢው ሳይሆን ከመርከቡ ነው ያሉት የሥራ ሃላፊዎቹ ካሳ ያልጠየቅንበትም ምክንያት ይሄው ነው ብለዋል፡፡

የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ ግን ተበላሽቷል ተብሎ የተቀበረው ስኳር በመጠን እጅግ ብዙ በመሆኑ፣ ካሳም ስላልተጠየቀበት፣ ማስረጃም ስላላገኘን መላ ሊባል ይገባዋል ብለዋል፡፡

(ትዕግስት ዘሪሁን)

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.