ሶማሊ ክልል የተሠራው ዘግናኝና አረመኔያዊ ሥራ ነው፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/40534


ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ሶማሊ ክልል የተሠራው ዘግናኝና አረመኔያዊ ሥራ ነው፡፡ ሰውን በቁሙ ማቃጠል፡፡ ሴቶችን መድፈር፡፡ መኪና ይዞ በየቤቱ እየዞሩ የሰው ንብረት መዝረፍ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል፡፡ ለመሆኑ መንግሥት የለም?
አንድ ክልልስ ሥልጣኑ የሰው ዘርን እስከማጥፋት ድረስ ነው? ይህን መሰሉ ግፍ ዚያድባሬ ኢትዮጵያን የወረረ ጊዜ ነበር በምሥራቁ ክፍል የተፈጸመው፡፡ ዚያድባሬ አለ ማለት ነው? የክልሉ ፕሬዚዳንት የልቡን ከሠራ በኀላ ትናንት ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መጥቶ እንመካከር ሲል ነበር፡፡
ሰው ከተቃጠለ፡ ንብረት ከተዘረፈ፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠለ በኀላ የምን ምከከር ነው? አሁን በዚያ ክልል ስላለው ሕዝብ እንደ አዲስ ማሰብ አለብን፡፡ ሌላ መፍትሔም ማምጣት አለብን፡፡ ከተቃጠለው ሕዝብ ይልቅ የአቃጣዩ አያያዝ በሚያስጨንቃቸው ሰዎች ሥር መኖር ከባድ ነው፡፡
በሰሞኑ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.