ሶስተኛው የሰላም የእግር ጉዞ በድሬዳዋ ይካሄዳል

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%88%B6%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8A%9B%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%88%9D-%E1%8B%A8%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%88%AD-%E1%8C%89%E1%8B%9E-%E1%89%A0%E1%8B%B5%E1%88%AC%E1%8B%B3%E1%8B%8B-%E1%8B%AD/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከአርቲስቶች ጋር በመተባበር የሰላም የእግር ጉዞ ማዘጋጀቱ ተገለፀ።

በሰላም የእግር ጉዞው ላይ የደም ልገሳ፣ የችግኝ ተከላ፣የፖናል ውይይት እንደሚካሄድም ነው የተነገረው።

ይህ የእግር ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን፥ ከዚህ በፊት በቡታ ጅራ፣ በሚዛን አማን ከተማ መካሄዱ ተጠቁሟል።

በቀጣይም በሌሎች ክልሎች የሚካሄድ መሆኑ በዛሬው ዕለት በተሰጠው መግለጫ ላይ ተጠቁሟል።

የጉዞው አላማ ስለመተባበር፣ ፍቅር፣ አንድነት እና መደመር ፅንስ ሃሳብ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን የፕሮግራሙ አዘጋጆች ገልፀዋል።

በሲሳይ ጌትነት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.