ሶስተኛው የአለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በቦነስ አይረስ ተጀመረ

Source: https://fanabc.com/2018/10/%E1%88%B6%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8A%9B%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%9D-%E1%8B%88%E1%8C%A3%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A6%E1%88%8A%E1%88%9D%E1%8D%92%E1%8A%AD-%E1%8C%A8%E1%8B%8B%E1%89%B3/

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስተኛው የአለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በታላቅ ድምቀት ተጀመረ።

ሁለተኛው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ልዑክ (የአትሌቲክስ ቡድንም) ትናንት ቦነስ አይረስ ደርሶ ዛሬ ልምምድ ጀምሯል።

በሶስተኛው የአለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ206 ሀገራት የተውጣጡ 4 ሺህ አትሌቶች በ32 የስፖርት አይነቶች ይሳተፋሉ።

ውድድሩ ከዚህ ቀደም ሲንጋፖር እና ቻይና ላይ ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ሁለቱም ጨዋታዎች ተሳትፋ ጥሩ ውጤት በማግኘት ተስፋ የሚጣልባቸውን አትሌቶችም ማግኘት ችላለች።

 

መረጃውን ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የፌስ ቡክ ገጽ አግኝተነዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.