ሽሽት እና የአባዱላ ገመዳ ነገር | ክንፉ አሰፋ

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81328

ከሰሜን እና ከበስተ-ምስራቅ አቅጣጫ እየነፈሰ ያለው አውሎንፋስ መርከብዋን እያናጋት ይገኛል። ጫፍ ላይ ጉብ ያሉትን አስተናጋጆች እያንጠባጠበ የሚገፋው ሃይል እየበረታ መጥቶ፣ አሁን ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ይመስላል። ይህ ሁላችንንም የሚያስማማን መራራ ሃቅ ነው። ችግሩ እዚህ ላይ አይደለም። ግን… እየሰመጠ ካለው ከዚህ መርከብ ለማምለጥ የተገኘችውን ቀዳዳ እየተጠቀሙ የሚሾልኩትን ሁሉ “ጀግና” ብለን ለመጥራት እንደምን ይዳዳን? ራስን ማዳን እና […]

Share this post

One thought on “ሽሽት እና የአባዱላ ገመዳ ነገር | ክንፉ አሰፋ

 1. ___ አባ ዱላ ትርጉሙ ባይገባኝም “ዱላ ከእጃቸው የማይጠፋ ሽማግሌ አባት ይመስለኝ ነበር። እኝህ ሰው ለዲሞከራሲ ብሔርተኝነት ሲባል የቀድሞው ደርግ ወታደር ምርኮኛ ምናሴ ተክለሃይማኖት በኋላ አባዱላ ገመዳ በጦር ጄኔራልነት ተሾመው የነበሩና በህወሃት ክፍፍል ወቅት ከውትድርናው ተነስተው የኦሮሚያ ፕሬዚዳትነት የተሾሙ ሲሆን፡ ሰውዬው በፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው በአቶ መለስ ባለመወደድ ከኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነት እንዲነሱ ተደርገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው የተሾሙ ናቸው።…
  አፈጉባኤ ማለት ፬፶፬ አባላት የተከበሩ ተብሎ በቀጭን ትዕዛዝ የተቀበሩ ለማለት ነው አደለም እንዴ?
  **ፈንቀሎ ያስወጣቸው የራሳቸው ጉዳይ እስኪመጣ ሕዝቤ እንዲህ ሲል ይቆዝማል። ለቀቁ..በረጅም ገመድ ታስረው ተለቀቁ ? በብቃት ማነስ ወደ ክልል ወረዱ? ኅይለመለስም ፓርቲዬ ከፈለገ ወረዳ እሄዳለሁ አላለምን? በግርግሩ ወቅት “ቤተመንግስት በር ላይ ደርሰናል!” ያሉት በፓርቲያቸው ስም ምንም ዓይነት መግለጫ እንዳይሰጡ፣ ከቤት እንዳይወጡና ሥራ እንዳይሠሩ ከተደረጉ ፩ዓመት ከ፱ ወር እንደተቆጠረ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ“ታፍኜ እቤት ውስጥ እንድቀመጥ ከተደረኩ በኋላ ተረስቻለሁ”–አሉ የአባ ዱላ አይሻሉም!? ህወሓት ውለታ አክባሪነቱን የኦነግ መሪዎች ለቅሶና ለፓርቲ ምሥረታ እንዲገቡ እንዲወጡ ማድረጉ ያስመሠግነዋል።
  ፩) አፈ ጉባኤው አባዱላ ገመዳ በኦሕዴድ ውስጥ በገነቡት ፈርጣም ኅይል በመተማመን እና የህወሓትን ኅይል መዳከም በማየት በምስራቅ ኢትዮጵያ ከ፻ሺህ በላይ የኦሮሚያ ተወላጆች ተፈናቃይ የሆኑበትን የሶማሌ ግጭትን በውጭ ሆነው ለመምራት ከማሰብ የመነጭ ነው ሲሉ…
  ፪) ምክንያት ደግሞ ገዢው የህወሓት ኅይል በስራ መልቀቅ ስም የተበላሸውን የኦሕዴድ ሥራን እንዲያፀዱለት ለማመቻቸት ነው ተብሎ ተገምቷል።
  ፫) አባዱላ ገመዳ ለኢህአዴግ ታማኝነታቸውን ያክል ግጭትና ፌደራላዊ በዓላት ባሉበት ሁሉ እንደሚላላኩትን ያህል ወደ ዲያስፖራ ጽንፈኛ ብሔርተኞች አቅንተው በህወሓት ላይ ምንም ተቃወሞ እንዳያሰሙ ምን ይደረገላችሁ? ሲሉ ለህወሓት ይዘው የመጡትን የአዲስ አበባ ከተማ አለመስፋፋት!፡ የፊንፊነ የኦሮሚያ ናት!..ኦሮሚኛ የፌደራል ተደራቢ የሥራ ቋንቋ ይሁን! ጥያቄዎች ነበሩ የተሳካም የተሰኩበትም እንዳለ የፖለቲካው ተንታኝ ጀዋሪው አብሮ እንደሚሰራ ሰሞኑን መስከሯል። አባዱላ ለቀቀ ማለት ፌደራሉ ፈረሰ የሚሉም አድናቂዎች በዝተዋል። ያ ማለት እንደበቀለ ገለባና መራራ ጉዲና መሰከሩበት እንጂ አላስተባበሉለትም። ኦሚኔ (ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ) በአባዱላ ተጠልፏል ሲል የአብዲ ፊጤን ፎቶ ከአባዱላ አያይዞ የመሠከረው የዲሲ ኦሮሞ ዜግነት ያለው ተስፋዬ ግብረእባብ(ገዳ) ነበር።

  ** የዚህ ሰሞን የከጅዎች ቁጥር መበራከት ተዓምር አደለም! “እየሰደቡ፡ እየተፉብኝ፡ ውስጥ ውስጡን በሲቪል ሰርቪስ ብዙ ነገር ሠርቻለሁ (ሰርስሬአለሁ) ያለው ጁነዲን ሰዶ ኦህዴድ ውስጥ ድሮም አሁንም ማንም ምንም እንዳለሆነ ሲናገር፡ ለማ መገርሳን ዲሞክራሲ መኖሩን እራሱን በራሱ እንደሚመራ አስለፈለፉት በአፉ ልክ ፻፶ ሺህ ኦሮሞ ከሰው ሰፈር አፈናቀለና ጭራሽ የደርግ ሥርዓት ናፋቂ ተባለና አረፈው!። አብዲ ኢሌ የኦህዴድን የምርኮ አፈጣጠራቸውን ያውቀዋላ!!
  ይህ ከዳ፡ ወጣ፡ ገባ፡ የሚባል የተሰባበረ ዜና ኢህአዴግን የከዱ ከተራ ሠራተኛ፡የፓርቲ አባል፡የሰፈር ልጅ፡ መምህር፡ካደሬ፡ ዳኛ፡ ሳይቀር ያንኑ የህወሓትን ማኒፌስቶ(ሕገመንግስት) ከማቀንቀን ሌላ የሚሰሩት አለን? ይልቁንም እኛ ብንሆን መገነጣጠልን እናፈጥነው ነበር ሲሉ ይሰማሉ። ድንቄም ታጋይ!
  ” መለስ ኖረ አልኖረ..ፋጡማ ኖረች አልኖረች…ዘርይሁን ኖረ አልኖረ…ኢህአዴግ በጸና መሠረት ላይ ቆሟል”የነፍስ አባታቸው ስብሃት ነጋ ታዲያ አባዱላ ፓርላማ ኖረ አልኖረ፡ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ቤተመንግስት ተገኘ አልተገኘ… አዜብ ቤት አላት የላትም የትግራይ እንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ በፀና የህወሓት ቤተሰባዊ የወሮ በላ ቡድን ቁጥጥር ሥር ውሏል። አዳሜ ሰባራ ሸክላ ይቆጥራል ልበል!?

  Reply

Post Comment