በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያዋ የሆነችው ETRSS- 01 የተሰኘችው የመሬት ምልከታ ሳተላይት ከቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/184809

ነገ ጠዋት 21 ጊዜ የደስታ መድፍ ይተኮሳል!!!
በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያዋ የሆነችው ETRSS- 01 የተሰኘችው የመሬት ምልከታ ሳተላይት ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 12፡00 ሠዓት ላይ ወደ ጠፈር የምትመጥቅ ሲሆን ይህን ታሪካዊ ቀን በማስመልከት 21 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር በግልባጭ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል፤ በመሆኑም በሚተኮሰው መድፍ ድምፅ ህብረተሰቡ እንዳይደናገጥ ኮሚሽኑ ያስታውቃል፡፡
ETRSS-1
• የሳተላይቷ ጠቅላላ ከሸብደት 72 ኪሎ ግራም ሲሆን ነገ ታሕሳስ 10 ቀን 2012
ዓ.ም ከማለዳው 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ
ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ
ትላካለች፡፡

• ሳተላይቷ በተወነጨፈች በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የህዋ ጥግ ላይ የምሕዋር ቦታዋን ትይዛለች፡፡
• በኢትዮጵያ ና ቻይና መንግስት በጀት የተገነባችው የመረጃና ኮሙኒኬሽን ሳተላይት
የምትመጥቀው ከቻይና የጠፈር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው።
• ሳተላይቷ ለግብር፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመገናኛና
ቴክኖሎጂ ለመሳሰሉት አገልግሎት መረጃ ትሰጣለች፡፡
• የሳተላይቷ የመረጃ መቀበያ እንጦጦ ላይ የተሰራ ሲሆን ከማምጠቅ ስራው ጀምሮ ቁጥጥሩ ሙሉ ለሙሉ እንጦጦ ላይ በኢትዮጵያውያን ይከናወናል።
• እንጦጦ የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ እንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና
የምርምር ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግትት ተዘጋጅቷል፡፡
• ጣቢያው የሳተላይቷ ደህንነት ክትትል የሚደረግበትና ከሳተላይቷ የሚገኙ መረጃዎች
የሚሰበሰቡበት ነው፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.