በሃረር አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ባለሀብቶችና ተወላጆች ወደ ክልላቸው እየተመለሱ ነው

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%89%A0%E1%88%83%E1%88%A8%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%8A%AB%E1%89%A3%E1%89%A2-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8A%96%E1%88%A9-%E1%8B%A8%E1%89%B5%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%8B%AD-%E1%89%A3%E1%88%88%E1%88%80%E1%89%A5/

በሃረር አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ባለሀብቶችና ተወላጆች ወደ ክልላቸው እየተመለሱ ነው
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወኪላችን እንደዘገበው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶችና ነዋሪዎች ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ወደ ክልላቸው በመመለስ ላይ ናቸው። ህወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት ሊነሳ ይችላል በሚል ቅስቀሳ የትግራይ ተወላጆች ከአካባቢው እንዲለቁ ማድረጉን የሚገልጸው ወኪላችን፣ ይህንን በማመን ባለፉት 3 ሳምንታት በርካታ ባለሀብቶች መውጣታቸውን ገልጿል።
በህወሃት በኩል የተለቀቀው መረጃ እውነት ይሁን አይሁን ሳይታወቅ፣ የትግራይ ተወላጆችን በማስፈራራት ከተለያዩ አካባቢዎች እንዲለቁ መደረጉ ፣ አብሮ በኖረው ህዝብ ላይ ቅሬታ ለመፍጠር እንዲሁም የትግራይ ህዝብ የደህንነት ዋስትና እንዳይሰማው በማድረግ ከጎኑ አሰልፎ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም የሚጠቀምበት ስልት በማለት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩ ገልጿል።
እስካሁን ድረስ በከተማው ይህ ነው የሚባል ችግር በትግራይ ተወላጆች ላይ አለመድረሱንመ አክሎ ገልጿል።

The post በሃረር አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ባለሀብቶችና ተወላጆች ወደ ክልላቸው እየተመለሱ ነው appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.