በሃረር ከፍተኛ የውሃ እጥረት ተፈጠረ

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%89%A0%E1%88%83%E1%88%A8%E1%88%AD-%E1%8A%A8%E1%8D%8D%E1%89%B0%E1%8A%9B-%E1%8B%A8%E1%8B%8D%E1%88%83-%E1%8A%A5%E1%8C%A5%E1%88%A8%E1%89%B5-%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%8C%A0%E1%88%A8/

በሃረር ከፍተኛ የውሃ እጥረት ተፈጠረ
( ኢሳት ዜና መስከረም 29 ቀን 2011 ዓ/ም ) ነዋሪዎች እንደገለጹት ቀደም ብሎ በፈረቃ ይሰጥ የነበረው ውሃ ሳይቀር በመቋረጡ፣ ህዝቡ የጉድጓድ ውሃ ለመጠቀም እየተገደደ ነው። ለመጠጥም ይሁን ለስራ የሚሆን ውሃ መጥፋቱን የሚገልጹት ነዋሪዎች ሁነታው እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ መንግስት አፋጣኝ መልስ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የውሃ ቴክኒክ ሃላፊው አቶ አዲል ችግሩ የተፈጠረው በመብራት እጥረት መሆኑን ገልጸዋል። የሃረርን ውሃ አቅርቦት ለማስተካከል አዳዲስ ጉድጓዶች የተቆፈሩ ቢሆንም፣ በየጊዜው የሚታየው የመብራት መጥፋትና የትራስፎርመር ችግር ውሃ ለማቅረብ እንዳላስቻላቸው ገልጸዋል።

The post በሃረር ከፍተኛ የውሃ እጥረት ተፈጠረ appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.