በሃና ማርያም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ ነው

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%89%A0%E1%88%83%E1%8A%93-%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%9D-%E1%89%A0%E1%88%BA%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%89%86%E1%8C%A0%E1%88%A9-%E1%89%A4%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%8B%A8/

በሃና ማርያም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ ነው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የቤት ማፍረስ ዘመቻን ተከትሎ እስካሁን ከ20 ሺ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ መጠለያ የቀሩ ሲሆን፣ ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ ያደረጉ ነዋሪዎች ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ብዙዎቹ መደብደባቸውንና እስካሁን 2 ሰዎች መገደላቸውንና ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንደኛዋ ቤቷ ሲፈርስ እቃዋን ለማውጣት ስትገባ ቤቱን በላዩዋ ላይ አፍርሰው የገደሏት ሲሆን፣ አንደኛው ደግሞ በጥይት ተመትቶ መሞቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ጥያቄያቸውን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያቀርቡም መልስ የሚሰጣቸው አላገኙም። ጠ/ሚኒስትሩን ለማናገር ሙከራ አድርገው የሚያቀርባቸው ሰው ማጣታቸውንም ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።

The post በሃና ማርያም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ ነው appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.