በሃዋሳ ከተማ የዝርፊያና ስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ 194 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%89%A0%E1%88%83%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%8B%A8%E1%8B%9D%E1%88%AD%E1%8D%8A%E1%8B%AB%E1%8A%93-%E1%88%B5%E1%88%AD%E1%89%86%E1%89%B5-%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%80%E1%88%8D/

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ የዝርፊያና ስርቆት ወንጀሎች ላይ ሲሳተፉ የነበሩ 194 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በትናትናው ዕለት በከተማዋ በሚገኙ ስምንት ክፍለ ከተሞች የፀጥታ አካላት ከማህበረሰቡ ጋር በሰሩት የተቀናጀ ስራ የተለያዩ የስርቆት ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 194 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወልደገብርኤል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ሞተር ሳይክሎችን በመጠቀም በከተማዋ የተለያዩ የስርቆትን ዝርፊያ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ ናቸው።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ወንጀሉን ለመፈፀም ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 122 ታርጋ የሌላቸው ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ።

ከዚህ ባለፈም በከተማዋ ነዋሪዎች በተደረገ ጥቆማ 4 መኪና የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል።

ማህበረሰቡ ተጠርጣሪዎችና ህገ ወጥ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረገውን አስተዋፅኦ ያደነቁት ኮሚሽነሩ፥በቀጣይም መሰል ተግባራትን ለመከላከል ከፖሊስ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በኃይለየሱስ መኮንን

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.