በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል! – ኢዜማ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/140087

አለምን ያስደመመ የስልጣኔ ፋና ወጊ የሆኑ የቁሳዊ፣ ባህላዊናሐይማኖታዊ እሴቶች ባለቤት የሆነችው አገራችን የብዙ ሺህ ዓመታትዝክረ-ታሪክም ለእኛ ለዜጎቿ ታላቅ ኩራት ነው፡፡በርካታ የታሪክ ቅርሶችዋ የሥልጣኔን የትየሌለነትንአጉልተው የሚዘክሩ ናቸው፡፡ኢትዮጵያበርካታ ብሄረሰቦቿ በፈጠሩት ማኅበራዊ መስተጋብር የተዋበች፣ የተለያዩ ሐይማኖች በመቻቻል፣ በመተሳሰብ ተደጋግፈው ኩራት የሆኗትታሪካዊት ሀገር ናት፡፡
ዜጎቿ የባህል፣የሐይማኖት፣ የቋንቋ እና የዘር ወዘተ … ልዩነቶቻቸው ለኢትዮጵያዊነታቸው ልዩ ውበት እንጂ ጋሬጣ ሆኖባቸው አያውቅም ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ሉዓላዊነት ከውጭ ወራሪ ኃይል ለመከላከል የውስጥ ልዩነቶቻቸውንአቻችለውበአንድ ረድፍ ስለመሰለፋቸው በታሪክ ድርሳናት ተከትበው የሚገኙ ናቸው፡፡ ይህ አኩሪ የሆነ ታሪካቸው ሳይሸረሸር ለቀጣዩ ትውልድይተላለፍ ዘንድ ዛሬ ላይ እየታዩ ያሉ ችግሮችን ማረቅ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የተለያዩ ሐይማኖት ተከታዮች እርስበእርስ በመደጋገፍ እና በመፈቃቀር የሚኖሩባት አገር መሆንዋ እሙን ነው፡፡ ክርስቲያኖች ከሙስሊሞች ሙስሊ.ሞች ከክርስቲያኖች ጎን በመቆም ሃዘንና ደስታን በጋራ የሚጋሩባት ምድር እንጂ እርስ በእርስየሚቆራቆሱባት አገር አይደለችም፡፡ አንዱ ሐይማኖት ለሌላኛው የቅርብ አጋርና ተቆርቋሪ በመሆን ኢትዮጵያዊነትን ያደምቃሉ እንጂበጠላትነት አይፈራረጁም፡፡
ይሁን እንጂ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በነበረው የፖለቲካ ትኩሳት ዘርና ቋንቋን ተገን አድርጎ በዜጎች መሀከል የተለኮሰው እሳትወላፈኑ ተፋቅረውና ተከባብረው ይኖሩ የነበሩ ሐይማኖቶችን ማወኩን ተመልክተናል፡፡ በአዲስ አበባ፣ ሶማሌ፣በኦሮሚያ፣በደቡብና በአማራ ክልሎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣መስጂዶችና ፀሎት ቤቶች ላይ የደረሱ ጥቃቶች የታሪካችን ማፈሪያ መሆናቸውን ልናስተውል ይገባል፡፡ በጅግጅጋ እና በሲዳማ ዞን ወረዳዎች በቅርብ ተከስተው በነበሩ ግጭቶች በርካታየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውና መፈራረሳቸው የአገሪቱን መፃኢ እድልና ህልውና ሊፈታተን እንደሚችል ማመን ይኖርብናል፡፡ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ የሚፈጠረው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.