በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘው ሰው ቁጥር ከ 5 ሚሊየን አለፈ

በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘው ሰው ቁጥር ከ 5 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘባት ሰው ቁጥር ከ5 ሚሊየን ማለፉን አስታወቀች፡፡

በህንድ የተመዘገበው ይህ ቁጥር ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ አገራት መካከል ሁለተኛዋ ያደርጋታል፡፡

በሀገሪቱ ከቅርብ ቀናት ወዲህ በየዕለቱ 90 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ እየተየዙ ይገኛሉ፡፡

ይህም በዓለም ላይ ቫይረሱ እጅግ በፍጥነት እየተስፋፋባቸው ከሚገኙ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ አድርጓታል፡፡

ቫይረሱ እንዲህ ሊሰራጭ የቻለው ጥላ የነበረውን እገዳ ማንሳቷን ተከትሎ መሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

እስከአሁን በሀገሪቱ በቫይረሱ አማካኝነት 80 ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ሆኖም የሞት መጠኑ ከተያዘው ሰውና ከሌሎች አገራት አንጻር ሲታይ አነስተኛ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ህንድ በየዕለቱ ከአንድ ሚሊየን በላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እያካሄደች መሆኑን ገልጻለች፡፡

 

ምንጭ፦ቢቢሲ

The post በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘው ሰው ቁጥር ከ 5 ሚሊየን አለፈ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply