በህግ ወጥ መንገድ የከበሩ ወንጀለኞችን በነፃ መልቀቅ ለህግ የበላይነት እና ፍትህ ጠንቅ ነው!

Source: https://ethiothinkthank.com/2019/08/14/releasing-illegal-profiteers-is-a-danger-to-justice/

ፀሐፊ፦ ሃኒባል ዘአዲስ አበባ

የግለሰቡ ስም አብይ አበራ ይባላል። በህገ ወጥ መንገድ ፣ የሀገርና የህዝብ ሀብት ከወያኔዎች ጋር የጥቅም ተካፋይ በመሆን የዘረፈ ፣ በርካታ ዜጎችን ደም እንባ ካስለቀሱ ወንጀለኞች መካከል አንዱ ነው። ሃቀኛ የሆኑ የህግ ተቋማት ባልደረቦች ባደረጉት ጥረት ፣ ይህ ግለሰብ በሚከተሉት ወንጀሎች አቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት ነበር። ገለሰቡ ከተከሰሰበት 40 በላይ የወንጀል ድርጊቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ፡ –

1. አራጣ ማበደር
2. የመሬት ወረራ መፈጸም
3. ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ማካሄድ
4. ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ማድረግ
5. ታክስ በማጭበርበር
6. ለምስክርት ሊቀርቡ ፈቃደኛ የሆኑ ዜጎች ላይ ያቀናበረው የግድያ ሙከራ ጥቂቶቹ ናቸው ።

አብይ አበራ የወያኔ ስርአት እጅግ አስከፊ ከሆኑት መገለጫዎች ውስጥ ተሳታፉ ከነበሩት ቀንደኞች አንዱ ነው። ሳይሰሩ ፣ሳይለፉ፣ በዘረፋ፣ የንጹጋ ዜጎች ሃብታን ንብረት በጉልበትና በማስፈራራት በመቀማት ፣ መሬት በመውረር፣ ሙሰኛና ስግብግ ባለስልጣኖችን በመወዳጀት በአቋራጭ መክበር የቻሉ፣ የደም ገንዘብ ያካበቱ (እንደ አሜሪካው robber barons, እንደጣልያኑ mafia) መሆኑ ብቻ አልበቃውም። ለህዝብ ነጻነት፣ ለፍትህ ፣ ለዴሞክራሲ ከስርአቱ የአፈናና የእመቃ ተቋማት እይታ ውጭ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በደህንነት መ/ቤቱ አፋኞች እንዲታደኑ በማድረግ፣ ለነጻነት ትግሉ እርዳታ በማድረገ ላይ የነበሩትን ለማሳደን ያደረገውን የክህደትና የነውር ተግባር በፋና ሬድዮ በድፍረት የተናገረ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ዜጎች በምሬት የሚያነሱት ጉዳይ ነው።

ይህም ብቻ አይደለም፣ አብይ አበራ በመባል የሚታወቀውና የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት የሆነው ይህ ስው ለሀገራችን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት “ፍትህ ሳይሆን ገንዘብ ነው ወሳኝ ፣በገንዘቤ ፓሊስና ዳኞችን እገዛለሁ” ብሎ የሚያምንም ድንቁርናና እብሪት የተጠናወተው መሆኑንም ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ በሚገባ ያውቁታል። ለበርካታ አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው የህዝብና የሀገርን ሃብት ለግል መበልጸጊያ እንደተጠቀሙት እነ ጀ/ል ክንፈ ዳኘው መሰሎቹ፣ ሌሎች የሜቴክ ቱባ ቱባ ሙሰኞችን፣ እንዱሁም በንግድ እንቅስቃሴ ስም የሀገርና የህዝብን ሀብት በተባባሪነት ከወያኔዎች ጋር ሲዘርፉ እንደነበሩ “ነጋዴዎች”/ማፍያዎች አብይ አበራ በተከሰሰበት ወንጀሎች በህግ አግባብ መሰረት ቅጣቱን ማግኘት ነበረበት። በተቃራኔው ዛሬም ልክ እንደ ትላንቱ ፓለሲችና ዳኞችን ጉቦ ለመስጠት የዘረፈው ሃብት ስላስቻለው በነጻ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

እንደዚህ አይነት ወንጀለኞች ለሰሩት መጠነ ሰፊ የወንጀል ተግባሮች በህግ አግባብ ቅጣታቸውን ማግኘት ሲገባቸው፣ ከህዝብና ከንጹሃን ግለሰቦች በተዘረፈ ገንዘብ በሰጣቸው አቅምና በሙሰኛ የጥቅም ተካፋይ የመንግስት ባለስልጣኖች እንዲሁም የፍትህና የህግ ውስጥ በሚገኙ ሙሰኛ የጥቅም ተካፋይ አጋሮቻቸው በመተማመን በነጻ ለመዘዋወር ከቻሉ ብዙ መዘዝ ያለው ፣ ከባድ ዋጋም የሚያስከፍል ይሆናል። ይህ ሁኔታ ዛሬም እንደትላንቱ በዘረፋ፣ በሙስና፣ በህዝብና በሀገር ሀብት ራስን ማክበር ያበረታታል ፣ በህጉ መሰረት የሚሰሩ ፣ የሚለፉና ታታሪ የሆኑ ባለሃብቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተመሳስይ የህግ ጥሰት እንዲሰሩ የሚያበርታታ ይሆናል።

ለማንኛውም ህብረተሰብ ማህበራዊ ጤንነት፣ ለህግ የበላይነት፣ እንዲሁም ለፍትህ ዜጎች ያላቸው እምነት ይበልጡኑ የሚሸረሸርበትና በወያኔ ስርአት ተንስራፍቶ የነበረው ይህን እጅግ የዘቀጠ/የበከተም፣ አይን ያወጣ የማፍያ ተግባሮች ዝም የሚባሉበት፣ የሚበረታቱበት ሁኔታ ለሀገር እድገትና ለህዝብ ልማት፡ ለማህበራዊ ጤንነት ትልቅ ጠንቅ ሆኖ ይቀጥላል።

በአለፈው ስርአት በሰፊዎ ያየነው ዘግናኝና አሳፋሪ የዘረፋና የሙስና ባህል ዳግም የሀገራችን መገለጫ የሚያደርግ አንድምታ ይኖረዋል። በመሆኑም ይህ ግለሰብም ሆነ ሌሎች መሰል ወንጀለኞች ለሰሩዋቸው በርካታ ወንጀሎች ቅጣታቸውን እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢና ፍትሃዊ ነው። የህግ የበላይነት ማስከበር፣ የፍትህና የዳኝነት ተቋማት ላስቀመጧዋቸውና ህብረተሰቡ ለሚተዳደርባቸው ህጎች ታማኝነቱን ማረጋገጥ ሀቀኛ የሆኑ የፍትህ አካላትና አባላት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት ጉዳይ መሆን ይገባዋል።

አብይ አበራና መሰሎቹ በሀገርና በህዝብ ላይ በህግ ወጥ መንገድ የከበሩና በርክታ ወንጀሎች የፈጸሙ ግለሰቦች ለፍርድ ቀርበው ቅጣጣቸውን የሚቀበሉበት ሂደት በአስቸኳይ ማስጀመር ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ይህ ወንጀለኛ ገለሰብ ከእስር ቤት ወጥቶ እንዳሻው በነጻ እንዲንቀሳቀስ የተፈቀፈበት ሁኔታ መጣራት አለበት። ይህን የፈቀዱ የህግና የዳኝነት ስርአት ውስት የተሰገሰጉ ሙሰኞችም በህግ ሊጠየቁ ይገባል። ለማንኛውም ሀገር እድገትና የህዝብ ልማት ጠንቅ የሆነ ባህል ተመልሶ የሀገራችን መገለጫ የሚያደረግ ሁኔታ ከእንግዲህ ተቀባይነት አይኖረውም።

ተመሳሳይ ጉዳዮችን መረጃ እየሰበሰብን ወንጀሎችንና በጥቅምና በሙስና ከእነዚህ ጋር የተሳሰሩ የመንግስት ባለስልጣኖችን ማገለጥ እንደሚቀጥል ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ለማሳወቅ እንወዳለን ።


ከላይ የቀረበው ፅሁፍ የፀሐፊው “ሃኒባል ዘአዲስ አበባን” አመለካከት የሚያንፀባርቅ ነው። በመሆኑም በፅሁፉ የተነሳው ሃሳብና አመለካከት በምንም አግባብ የድረገፁን ወይም የአዘጋጆቹን አቋም አይወክልም።

አቶ ስዮም ተሾመ

የድረገጽ ዋና አዘጋጅ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.