በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች ሦስተኛ ዲግሪ ካላቸው መምህራን እኩል ገቢ ያገኛሉ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/154108

(ኢፕድ)
የአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች ለልመና በተሰማሩ ሰዎች መወረራቸው ለተመልካች ግራ የሚያጋባ ነው። እነዚህ ሰዎች የልመና ስልታቸው የተለያየ ሲሆን፤ በግጥምና በዜማ ፣ ጨቅላ ሕፃናትን በመታቀፍና በማስለቀስ፣ የሰውነት አካልን የመኪና ግራሶ በመቀባት ከፍተኛ ቁስለት ያለው በማስመሰል፣ ባስ ሲልም ከዚህ ቀደም በፖሊስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እንደተጋለጠው የውሻ ቡችላ ልጅ አስመስሎ በመታቀፍና የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የሚያከናውኑት ሆኖ ይስተዋላል፡፡
በማንኛውም ዘዴ ይሁን በልመና የሚሰበስቡት ገንዘብ ሳይሰሩና ሳይለፉ የሚገኝ በመሆኑ፤ እንዲሁም የየእለት ገቢው ሲጠራቀም ዳጎስ ያለ ስለሆነ ሙሉ አካል ያላቸውና ጤናማ የሆኑ፣ ሰርተው መብላት የሚችሉ ዜጎች እጃቸውን ለልመና ዘርግተው ሳንቲም ወደ ሚያስገኘው ዘርፍ መሰማራትን ምርጫቸው አድርገዋል፡፡
ለመሆኑ በርካታ ዜጎች ልመና ላይ ለምን ተሰማሩ? በቀን የሚያገኙት ገቢ ምን ያህል ነው? እነማን በልመና ላይ ተሰማሩ? ልመና የሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ ምንድን ነው? የሚለውን በዝርዝር ለማወቅ በልዩ ልዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጥናቶች ተደርገዋል፡፡
በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና መምህርና በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ስነልቦና የሦስተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጽሁፋቸውን በአዲስ አበባ በአስሩ ክፍለ ከተሞች “በጤናማ ለምኖ አዳሪዎች” ላይ እየሰሩ ያሉት አቶ አብዱሰላም ከማል፤ ስለለማኞች የገቢ መጠን ባደረጉት ጥናት ከዩኒቨርሲቲ መምህራን ዶክተሮችና ሚኒስቴሮች እኩል ወርሃዊ ገቢ እደሚያገኙ ተገንዝበዋል።

አንድ ጤነኛ ለማኝ ምንም ስራ አልሰራም ከተባለ በቀን ከ100 እስከ 200 ብር ያገኛል። ይህም አንድ ለማኝ በወር ምንም አልሰራም ከተባለ ዝቅተኛ ገቢው 3ሺ ብር መሆኑን ያሳያል። ጤነኛ ለማኞች የሚያገኙት ዝቅተኛ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ካለው የመንግስት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.