በመተከል ዞን የሚገኙ አምስት ወረዳዎች በኮማንድ ፖስት እንዲመሩ ተወሰነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል…

በመተከል ዞን የሚገኙ አምስት ወረዳዎች በኮማንድ ፖስት እንዲመሩ ተወሰነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች እየተከሰተ ባለው የጸጥታ ችግር ለንጹሃን ዜጎች ህይወት መጥፋትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ አካላትን በመለየት የክልሉ መንግስት ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ገልፀዋል፡፡ በዞኑ በወምበራና በቡለን ወረዳዎች ከተከሰቱት የጸጥታ ችግሮች ጋር ተያይዞ በጥፋቱ እጃቸው ያለበትን አካላት ለመለየት ጠንካራ ግምገማ መካሄዱን የገለጹት አቶ ጌታሁን፣ በጥፋተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ለህዝብም ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ በችግሩ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን የመርዳት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ጌታሁን አብዲሳ ገልጸዋል፡፡ የክልሉ ከፍተኛ የአመራሮችና የጸጥታ ሃይሎች ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት ችግሩን ለማስቆም እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ጌታሁን፣ የአካባቢውን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ/ም በዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ የጥፋት ሃይሎች በፈጸሙት ተመሳሳይ ጥቃት የ14 ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉንም ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው ሰላም ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ በመተከል ዞን የሚገኙ አምስት ወረዳዎች በኮማንድ ፖስት እንዲመሩ መወሰኑንም አስታውቀዋል፡፡ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን የሚደግፉና ከሰላማዊ ትግል ይልቅ የአፈሙዝ ትግልን የመረጡ አካላት ላይ የክልሉ መንግስት ከመከላከያ ሰራዊትና ከጸጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ጌታሁን አብዲሳ አሳስበዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply