በመተከል ዞን ጉባና ቡለን ወረዳዎች የተፈፀመውን ጥቃት የፀረ ለውጥ ኃይሎች የሆኑት ቤህነን፣ ጉህዴንና ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በህወኃት በመታገዝ እንደፈፀሙት ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በመተከል ዞን ጉባና ቡለን ወረዳዎች የተፈፀመውን ጥቃት የፀረ ለውጥ ኃይሎች የሆኑት ቤህነን፣ ጉህዴንና ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በህወኃት በመታገዝ እንደፈፀሙት ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በመተከል ዞን ጉባና ቡለን ወረዳዎች የተፈፀመውን ጥቃት የፀረ ለውጥ ኃይሎች የሆኑት ቤህነን፣ ጉህዴንና ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በህወኃት በመታገዝ እንደፈፀሙት ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ጥቃት የፈፀሙ የታጠቁ ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር የማዋሉና ተጎጂዎችን የማቋቋሙ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአማራ ክልል ሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡ የአማራ ክልል ሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ ስለተፈጸመው ጥቃት ሙሉ መረጃ ለማግኘት የፀጥታ አካላት አሁንም ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ገደቤ በመተከል ዞን ባለፉት ዓመታት ሲያጋጥሙ የነበሩ ጥቃቶች ሰላማዊ እንዲሆኑ ሁለቱ ክልሎች እና የመከላከያ ሠራዊት በጋራ ሲሠሩ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ‘‘በቅርቡ ከዚህ በፊት ግጭት ባልተከሰተባቸው በመተከል ዞን ጉባ እና ቡለን ወረዳዎች ላይ በታጣቂዎች ጥቃት ተፈጽሟል’’ ብለዋል፡፡ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ‘‘ጥቃቱ የፀረ ለውጥ ኃይሎች በሆኑት ቤህነን፣ ጉህዴንና ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በህውኃት በመታገዝ የፈጠሩት ነው’’ ብለዋል፡፡ አካባቢውን ለማረጋጋት እና ለተጎጂዎች አስቸኳይ እና ዘላቂ ድጋፍ ለማድረግ ከሁለቱ ክልሎች በተጨማሪ የፌዴራል መንግሥትና የመከላከያ ሠራዊት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ገደቤ ‘‘ከታጣቂዎቹ ጥቃትን የመፈጸም ባሕሪ አንጻር ተነስቶ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ስልቶችን በመንደፍ እየተሠራ ነው’’ ብለዋል፡፡ ‘‘ጥቃቱ በነዋሪዎች መካከል ወይም የሕዝብ ለሕዝብ አይደለም’’ ያሉት አቶ ገደቤ ‘‘ሀገሪቷ እንዳትረጋጋ በየወቅቱ በሽምቅ እየመጡ የሚያጠቁ ኃይሎች ሴራ ነው’’ ብለዋል፡፡ የሕዝቦችን አንድነት ለመሸርሸር አድፍጦ ጥቃት የሚፈጽመው ኃይል ለነዋሪዎች ስጋት እንዳይሆን የፀጥታና የመከላከያ ሠራዊት አሁንም በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ገደቤ ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ቀጣናው ሰላማዊ እንዲሆን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ በጉባው ጥቃት ላይ የተሳተፉ ታጣቂዎችን ‘‘በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል’’ ያሉት አቶ ገደቤ ቡለን ወረዳ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ኃይሎች ግን እስካሁን ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‘‘በጥቃቱ ሕይወታቸውን ያጡ፣ የተጎዱ፣ የተሰደዱ ሰዎችን መረጃ በተመለከተ የፀጥታ ኃይሉ አጣርቶ እስከሚያቀርብ ጊዜ መሥጠት ያስፈልጋል’’ ብለዋል አቶ ገደቤ፡፡ ለዚህ እንደምክንያት የጠቀሱት ‘‘ሕይወታቸው ጠፍቷል’’ ተብለው የተለቀሰባቸው ሰዎች ራሳቸውን ከጥቃቱ በማትረፍ ከነበሩበት ጫካ ወጥተው ወደቤታቸው እየተመለሱ መሆናቸውን ነው፡፡ በዞኑ ከዚህ በፊት በተፈጠሩ ግጭቶች ተፈናቅለው የነበሩ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች ወደቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉን ያስታወሱት አቶ ገደቤ አሁን በተፈጠረው ግጭት ምክንያት መፈናቀል እንዳይከሰትም በቅርበት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል። የአማራ ክልል ሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ ይህን ይበሉ እንጅ ከአደጋ ካመለጡ ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ከቤህነን፣ ጉህዴንና ኦነግ ሸኔ በተጨማሪ የመንግስት ታጣቂ የሆኑ ሚሊሻዎችም በጥቃት መሳተፋቸውን ያመለክታል። መከላከያ ሰራዊትም ሆነ የአካባቢው የፀጥታ አካላት የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን በዋናነት የአገው/አማራ ተወላጆችን ለመታደግ አለመቻሉንና ጥቃቱ ተፈፅሞ የበርካቶች ህይወት ከጠፋና ከተፈናቀሉ በኋላ በማግስቱ ጳጉሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ስለመድረሱ ነው ነዋሪዎች የተናገሩት። የፌደራል፣የአማራ ክልልና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የፀጥታ አካላት ተናበው እየሰሩ ነው ለማለት እንደሚቸግር ነው የደረሰን መረጃ ያመለከተው። ቀደም ሲል በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ 14 ንፁሀን የአማራ ተወላጆች በታጣቂዎች በጥይት መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ጳጉሜ 1 ቀን 2012 ዓ.ም በተፈፀመው ጥቃት ከመንግስት አካላት በትክክል ባይጣራም ከ80 በላይ አገው/አማራዎች በጥይትና በስለት ስለመገደላቸው ምንጮች ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply