በመንግሥት ላይ 11.9 ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ የተከሰሱ ኃላፊዎች ገንዘቡን በመመለሳቸው ክሳቸው ተቋረጠ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75407

Reporter Amharic
የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኃን በመምራት በመንግሥት ላይ ከ11.9 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ፣ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ከአንድ ዓመት በፊት ተመሥርቶባቸው የነበሩት፣ የቀድሞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፀዳለ ማሞን ጨምሮ የአራት ኃላፊዎች ክስ ተቋርጦ ከእስር ተፈቱ፡፡

ተከሳሾቹ ወ/ሮ ፀዳለ ማሞ፣ የጽሕፈት ቤቱ የሎጂስቲክስ አስተዳደርና ፋይናንስ መምርያ ኃላፊ የነበሩት አቶ የማነ ፀጋዬ፣ የመሬት ዝግጅት መሠረተ ልማትና ዲዛይን መምርያ ረዳት መምርያ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ሳባ መኮንንና የፕላንና ዶክመንቴሽን አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሽመልስ ዓለማየሁ ናቸው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የጽሕፈት ቤቱ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል ሆነው ሲሠሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዕቃና አገልግሎት ግዥ መመርያ ቁጥር 4/1991 አንቀጽ 6(2) እና አንቀጽ 25 በመተላለፍ ከተፈቀዱ የግዥ ዘዴዎች ውጪ እንዲፈጸም ጨረታ ማውጣታቸወን ዓቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት የመሠረተባቸው ክስ ያስረዳል፡፡ በመሆኑም የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ከየማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ጋር በመመሳጠር፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ያወጣውን ጨረታ እንዲያሸንፍና ግዥው እንዲፈጸም በማድረግ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንም ክሱ ያብራራል፡፡ ለአፈር ቆርጦ መጣል፣ ለገረጋንቲ ማጓጓዣና ለገረጋንቲ መሙላት 33,384,526 ብር ግዥ መፈጸሙንም ጠቁሟል፡፡ ይኼ ዋጋ የተከፈለው ሌሎች ተጫራቾች ካቀረቡት ዋጋ በላይ እጅግ በተጋነነና ከ80 እስከ 120 በመቶ ጭማሪ በማድረግ መሆኑንም አክሏል፡፡
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የ11,979,848 ብር ጉዳት በመንግሥት ላይ አድርሰዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸውና ዋስትና ተከልክለው ሲከራከሩ የከረሙ ቢሆንም፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በአዋጅ በተሰጠው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.