በመንግስት ወታደሮች ላይ በተከፈተ ጦርነት የሟቾች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ተነገረ

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/43834

አባይ ሚዲያ ዜና 

በሰሜን ጎንደር የመንግስት ወታደሮች እና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት ባደረጉት ውጊያ ህይወታቸውን ያጡ እንዲሁም የቆሰሉ ቁጥራቸው ሊጨምር እንደሚችል ተነገረ።

በተከፈተው ጥቃት የተጎዱ በቦታው ሰፍረው የነበሩ የመንግስት ታጣቂዎች ለህክምና ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ምንጮች ገልጸዋል።

በተከፈተባቸው ዘመቻ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው የአገዛዙ ወታደሮች ቁጥራቸው ወደ አስር ከፍ እንዳለ  የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በውጊያው ከመንግስት በኩል  በትንሹ ሰባት ወታደሮች መገደላቸው እየተነገረ ሲገኝ የተገደሉት ወታደሮች ቁጥር  እየጨመረ እንደሆነም  የሚገልጹ ተገኝተዋል።

ቁጥራቸው ከፍ ያለ ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸው በተነገረለት በዚህ ዘመቻ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት በኩል ስለደረሰ ጉዳት የሚገልጹ መረጃዎች አልተሰጡም።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባልተናሳበት በዚህ ወቅት በጎንደር አከባቢ በሰፈሩ የመንግስት ወታደሮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸው በአከባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ያሳይል ተብሏል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.