በመዲናዋ ለመብራትና ውሃ አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል ደንበኞች እየተጉላሉ መሆኑ ተገለፀ

Source: https://fanabc.com/2019/02/%E1%89%A0%E1%88%98%E1%8B%B2%E1%8A%93%E1%8B%8B-%E1%88%88%E1%88%98%E1%89%A5%E1%88%AB%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%8B%8D%E1%88%83-%E1%8A%A0%E1%8C%88%E1%88%8D%E1%8C%8D%E1%88%8E%E1%89%B5-%E1%8A%AD%E1%8D%8D/

አዲስ አበባ፣የካቲት 5፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የመብራትና ውሃ አገልግሎት ክፍያን ለመክፈል ደንበኞች እየተጉላሉ መሆኑ ተገለፀ።

ደንበኞች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የመብራትና የውሃ አገልግሎት ክፍያን ለመክፈል ጣቢያዎች በሚያቀርቧቸው የተለያዩ ችግሮች ሳቢያ  እየተጉላሉ መሆኑን ተናግረዋል ።

ጣቢያቸን ከትናንት ጀምሮ በተለያዩ የክፍያ ጣቢያዎች ተግኝቶ ባደረገው ምልከታ ፥ከሶስት በላይ የክፍያ ጣቢያዎች በኔትወርክና ጄኔሬቴር መቋረጥ ምክንያት  አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

በአንዳንድ ጣቢያዎች በተከሰተው ጊዜያዊ ችግር  ምክንያት  ደንበኞች ምንም አገልግሎት ሳያገኙ እንዲመለሱ መደረጉን ታዝበናል።

ከዚህ ባለፈም በመዲናዋ በሚገኙ የተወሰኑ የለሁሉ የክፍያ  ጣቢያዎች ላይ ደንበኞች ረጃጀም ሰልፎችን  ተሰልፈው ለማየት ተችሏል ።

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎትናየ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበኩላቸው በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ብለዋል።

እስከ ሰኔ ወር ባለው የለሁሉ ውል ክፍያ ችግር እንዲቀረፍ እየተሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ከሰኔ በኋላ በሚኖር ክፍያም በራሳቸው አገልግሎቱን ለማፋጠን ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል ።

 

በታሪክ አዱኛ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.