በሙስና ተዘፍቀዋል የተባሉ የኢትዮቴሌኮም ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተከሰሱ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/131817

Reporter Amharic

ከ295.2 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረሳቸው  በክሱ ተጠቁሟል
የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አማረ አምሳሉንና በእስር ላይ የሚገኙትን አቶ ኢሳያስ ዳኘውን ጨምሮ፣ አሥር ከፍተኛ ኃላፊዎች ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
ተከሳሾቹ ሥልጣናቸውን ያላግባብ ተጠቅመው ተፈጽሟል ከተባለው ወንጀል ድርጊት ከሚገኘው ጥቅም ቀጥተኛ ተካፋይ በመሆን 295,586,120 ብር ጉዳት አድርሰዋል በማለት፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ያቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡
ዓቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ሁለት ክሶች አቅርቧል፡፡ በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል በማለት በክሱ ያካተታቸው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ አማረ አምሳሉ፣ የኤንጂፒኦ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወልደ ጊዮርጊስ ወልዱ፣ በእስር ላይ የሚገኙትና የአፕሊኬሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው፣ የኔትወርክ ኢንፍራስትራክቸር ፕሮግራም ዳይሬክተር የነበሩት አቶ አብዱልሀፊዝ አህመድ፣ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ፕሮጀክት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ማስረሻ ጥላሁን፣ የኢንተርፕራይዝ ማኔጅመንት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሰይፈ ኃይለ ሥላሴ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የኦፕሬሽን ሰፖርት ኦፊሰር የነበሩት አቶ ፀጋዬ መኮንን፣ የኤንጂፒኦ ምክትል ፕሮግራም ዳይሬክተር የነበሩት አቶ አይተንፍሱ ወርቁ፣ የሲቪል ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ጌታሁን ያሲንና የኤንጂፒኦ ሞባይል ፕሮግራም ኃላፊ የነበሩት አቶ ሳሙኤል ፈጠነም በክሱ ተካተዋል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው ተከሳሾቹ በ1996 ዓ.ም. የወጣ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ) እና 407 (1ሀ እና ለ) እና (3) ላይ ተደነገገውን በመተላለፍ፣ ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል፡፡ ከአቶ አማረ እስከ አቶ አይተንፍሱ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.