በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ የጣና ሃይቅ ሞልቶ ባጥለቀለቃቸው በአራት ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ የጣና ሃይቅ ሞልቶ ባጥለቀለቃቸው በአራት ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ የጣና ሃይቅ ሞልቶ ባጥለቀለቃቸው በአራት ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወረዳው አቸራ ቀበሌ የሀይቁ ሞልቶ መፍሰስ ባደረሰባቸው ጉዳት ቤታቸውን ጥለው በመውጣት በአምብል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተጠልለው ካገኘናቸው ነዋሪዎች ውስጥ አንዱ የሆኑት አርሶ አደር ውሃው አካባቢያችን ላይ ጉዳት ካደረሰብን ጊዜ ጀምሮ በዚሁ ት/ቤት ተሰብስበን የምንገኝ ሲሆን በውሃው መጥለቅለቅ በአካባቢው በሚገኙ የውሃ ተቋማት ላይ ጉዳት በመድረሱ የንፁህ መጠጥ ውሃ ለማግኘት ተቸግረናል ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም ለውሃ ወለድ በሽታዎችና ለመሰል የጤና ችግሮች መጋለጣቸውን ገልፀዋል፡፡ ስለጉዳዩ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አደጋ መካከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ ችግሩ መኖሩን ጠቁመው የውሃ ማከሚያ መድሃኒቶች መላኩን አስታውቀዋል፡፡ ሃላፊዋ አያይዘውም በጣና ምክንያት ችግር የደረሰባቸው ወገኖች ወደ ቀደመ ህይወታቸው እስኪመለሱ ድረስ በዘላቂነት የንፁህ መጠጥ ውሃ ለማቅረብ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን ስለመባሉ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮምኒኬሽን ዘገባ አመልክቷል። ከባድ የክረምት ዝናብ እያስከተለ ባለው መጥለቅለቅ፣ጎርፍ፣የመሬት መሰንጠቅ በተለይ በአፋር፣በአማራና በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የሰው ህይወት፣የንብረትና የሰብል ውድመት እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል። በአማራ ክልል ደግሞ በሰሜን ሸዋ፣በምስራቅ ጎጃም፣በሰሜንና በደቡብ ጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉ ይታወሳል። ከጣና ሀይቅ ሞልቶ መፍሰስ ጋር በተያያዘ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ በሚገኙ 5 ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የሩዝ ሰብላቸው ከጥቅም ውጭ መሆኑንና መንግስትም ከአካባቢው እንዲወጡ ብሎም ከምግብና ውሀ አቅርቦት ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ አይደለም ሲሉ በተለይ በፎገራ የዋገጠራ ቀበሌ ነዋሪዎች ቅሬታ ማቅረባቸውን የአማራ ሚዲያ ማዕከል መዘገቡ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply