በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ደጀን አግሮ ቢዝነስ በሚል ስያሜ የተቋቋመው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተረከበውን መሬት ለማልማት በገባው ውል መሠረት ወደስራ አለመግባቱ ተገለፀ።…

በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ደጀን አግሮ ቢዝነስ በሚል ስያሜ የተቋቋመው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተረከበውን መሬት ለማልማት በገባው ውል መሠረት ወደስራ አለመግባቱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ወረዳ ደጀን አግሮ ቢዝነስ በሚል ስያሜ የተቋቋመው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከ30 ሄክታር መሬት በላይ ተረክቦ ለማልማት በገባው ውል መሠረት ወደስራ አለመግባቱን ተሸሽሎ በወጣው መመሪያ ቁጥር 12 የተቋቋመው የወረዳው የኢንቨስትመንት ቴክኒክ ኮሚቴ ገልጧል፡፡ የወረዳው የኢንቨስትመንት ቴክኒክ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ለውጤ አንዷለም ባለሀብቱ በእንስሳት እርባታም ይሁን በሰብል ልማት በተሰማራበት ዘርፍ ከአርሶ አደሩ በተሻለ ሊያስተምርና አርኣያ በመሆን እየሰራ አይደለም ብለዋል፡፡ የተረከቡትን መሬት በእንስሳት መኖም ይሁን በሰብል ልማት በተሻለ መልኩ ማልማት ሲገባቸው ያዘመሩት አዝመራ በመጤ አረም የተወረረ መሆኑን ተናግረዋል። በምስራቅ ጎጃም ዞን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የግብርና ነክ ኢንቨስትመንት ባለሙያና የቴክኒክ ኮሚቴው አባል አቶ አዲሱ ንጉሴ ደጀን አግሮ ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዛሬ 13 ዓመት በፊት በእንስሳት እርባታ ፣ በሰብል ልማት፣ በደን ልማትና በንብ ማነብ የሥራ ዘርፍ እንደተሰማራ ያቀረበው ፕሮጀክት ቢገልጽም መሬቱን አጥሮ ከማስቀመጥ በዘለለ በገባው ውል መሠረት አንድም ስራ እንዳልሰራ ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ አዲሱ ገለፃ ኮሚቴው ባደረገው ምልከታ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው የተወሰነ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ በላይ ድርጅቱ ላለፉት በርከካታ አመታት ይፈፀሙ የነበሩ አስተዳደራዊ በደሎች በመኖራቸው ወደስራ ለመግባት እንቅፋት ሆኖባቸው እንደቆየ ገልጸው የመብራትና የውህ መሰተ ልማቶች አለመሟላት ለፕሮቸክቱ የስራ እንቅፋት ሆኖ መቀየቱን ተናግረዋል፡፡ ቀጣይ መንግስት አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ከደገፈ ወደስራ እንደሚገቡም ጠቁመዋል ያለው የደጀን ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply