በምንጃር ሸንራ ወረዳ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ተገለፀ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 7/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// በወረዳው የአረርቲ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ መስፍን…

በምንጃር ሸንራ ወረዳ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ተገለፀ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 7/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// በወረዳው የአረርቲ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ መስፍን አበበ ለአሻራ ሚዲያ እንደገለፁት የአንበጣ መንጋው ከ7 በላይ ቀበሌዎችን መውረሩን ተናግረዋል፡፡ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ለሀገሪቱ የጤፍ ግብዓት አቅራቢ ከሆኑ ቀዳሚ አካባቢዎች አንዱ ቢሆንም በተከሰተው የአንበጣ መንጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዳ ነው ብለዋል፡፡ ዛሬ ጥቅምት 7/2013 ዓ.ም በአንድ አውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ማካሄድ ቢጀመርም ከኮምቦልቻ ነዳጅ ቀድቶ ለመመለስ በሚወስደው ረጅም ጊዜ የተነሳ የመከላከል ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል፡፡ የአንበጣ መንጋው በአጭር ጊዜ በመስፋፋት ‹‹መተህ ብላ›› የተሰኘ አጎራባች ወረዳ ላይ መከሰቱንም አስረድተዋል፡፡ ከኬሚካል ርጭቱ ባሻገር ማህበረሰቡ ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመተባበር በከፍተኛ ሁኔታ ለመከላከል ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። የፌደራል መንግስትም የአንበጣ መንጋው የደረሰበትን አስቸጋሪ ሁኔታ በመረዳት ፈጣን ምላሽና የመፍትሄ አማራጮችን እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡ ዘጋቢ፡በረከት የሽዋስ

Source: Link to the Post

Leave a Reply