በሞባይል ስልክ የፅሑፍ መልዕክት መለዋወጥ ማዘውተር ሲጋራ ማጤስን ለማቆም ይረዳል

Source: https://fanabc.com/2018/12/%E1%89%A0%E1%88%9E%E1%89%A3%E1%8B%AD%E1%88%8D-%E1%88%B5%E1%88%8D%E1%8A%AD-%E1%8B%A8%E1%8D%85%E1%88%91%E1%8D%8D-%E1%88%98%E1%88%8D%E1%8B%95%E1%8A%AD%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%88%88%E1%8B%8B%E1%8B%88/

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 11፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሞባይል ስልኮች የፅሑፍ  መልዕክት መለዋወጥን ማዘውተር ሲጋራን ለማቆም የሚረዳ መሆኑን ጥናት አመለከተ።

በትናንትነው ዕለት በቻይና ተመራማሪዎች ይፋ የሆነው ጥናት እንደሚያመላክተው በሞባይል ስልኮች አዘውትሮ  የፅሁፍ መልዕክት መለዋወጥ ሲጋራ ማጤስን ለማቆም ሁነኛ መፍትሄ መሆኑ ተረጋግጧል።

በምርምሩ ሂደት በናሙና የተመረጡ 1 ሺህ 369 የሲጋራ ሱስ ተጠቂ  የሆኑ የቻይና ወጣቶች ላይ ለ12 ሳምንታት የቆየ ጥናት ተካሂዷል።

በጥናቱ ወቅትም ተጠቂዎቹ በሚያጨሱብት ጊዜ በሞባይል ስልኮቻቸው ላይ የተለያዩ የፅሁፍ መልዕክቶች በመላክ እንዲረበሹ ይደረጋል።

ከ12 ቀናት ቆይታ በኋላም 89 የሚሆኑት የሱሱ ተጠቂዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ማጨስ ያቆሙ ሲሆን፥ 82 የሚሆኑት ደግሞ ከፍተኛ በሆነ ደረጃ ሱሱን ለመቀነስ ችለዋለል።

ሌሎች 26 የሚሆኑ የሱሱ ተጠቂዎች ደግሞ ከችግሩ ለመላቀቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ  ላይ መሆናቸው ነው የተገለጸው።

ይህ ውጤትም በሲጋራ ሱስ የተጠቁ ሰዎችን የምክር አገልግሎት በመስጠት ድርጊቱን እንዲያቆሙ ከማድረግ በብዙ እጥፍ የሚሻል መሆኑን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል ።

በቻይና ሲጋራ በብዛት ከሚጤስባቸው ሀገራት ቀዳሚዋ ስትሆን በዓለም 40 በመቶ የሚሆኑት አጫሾች የቻይና ዜጋዎች መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ ፦ሲጂቲኤን

Share this post

One thought on “በሞባይል ስልክ የፅሑፍ መልዕክት መለዋወጥ ማዘውተር ሲጋራ ማጤስን ለማቆም ይረዳል

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.