በራይድ እና ዛይ ራይድ መካከል ውዝግብ ተነስቷል

Source: https://mereja.com/amharic/v2/149823

በራይድ እና ዛይ ራይድ መካከል ውዝግብ ተነስቷል!
በራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እና ዛይ ራይድ ሜትር ታክሲ መካከል ከንግድ ስም ባለቤትነት እና ከፈጠራ ባለቤትነት መብቶች ጋር በተያያዘ በተነሳው ውዝግብ ራይድ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ምርመራ ተጀመረ።
ከአራት ወራት በፊት ራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት የስያሜው የባለቤትነት መብት ይገባኛል በሚል ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት እና ለንግድ ውድድር እና ሸማቾች መብት ጥበቃ ባለሥልጣን ማመልከቻ ማስገባቱን ተከትሎ ነው ምርመራው የተጀመረው።
‹‹ራይድ›› የሚለው ቃል በራሱ አገልግሎትን የሚያመላክት ገላጭ ቃል እንጂ ስያሜ መሆን የሚችል ቃል አይደለም ያሉት የዛይ ራይድ ሜትር ታክሲ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሀብታሙ ታደሰ፣ ከራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት ከአንድ ዓመት ቀድመው ወደ ሥራ መግባታቸውን እና በዘርፉ መጀመሪያው መሆናቸውንም ይናገራሉ።
‹‹የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ለራይድ ከአንድ ዓመት በፊት የንግድ ስያሜ ባለቤትነት ማረጋገጫ መፍቀዱ አግባብ ያልሆነ መሆኑን እያወቅን፣ ያለው ገበያ ሰፊ መሆኑን ተከትሎ አብሮ ለመሥራት እና ለመነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም›› ሲሉም ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.