በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ተቃውሞ አሰሙ

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%8A%AB%E1%89%B3-%E1%8B%A8%E1%88%83%E1%8A%93-%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%9D-%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%8A%93%E1%89%83%E1%8B%AE%E1%89%BD-%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%89%A4%E1%89%B0/

በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ተቃውሞ አሰሙ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ከ3 ሺ የማያንሱ ቤታቸው የፈረሰባቸውና በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙት ዜጎች ወደ ቤተ መንግስት አምርተው ጉዳያቸውን ለጠ/ሚኒስትሩ ለማቅረብ ቢፈልጉም አልተሳካላቸውም። ይህን ተከትሎ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ ሲያመሩ የፌደራል ፖሊሶች መንገድ ላይ በመጠባባቅ ሰልፈኞችን አግተው ውለዋል። ፖሊሶቹ በሰልፈኞች ላይ ያደረሱት ጉዳት የለም።
ተፈናቃዮቹ ጥያቄያቸውን የሚሰማ አካል በማጣታቸው ሰልፍ ለማድረግ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

The post በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ተቃውሞ አሰሙ appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.