በሰላሳ ቀናት ውስጥ ሲኖዶስ መልስ ካልሰጠን አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን ሲል የኦሮሚያ ቤተክህነት ገለጸ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/142804

BBC Amharic
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት በክልል ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ቅዱስ ሲኖዶሱ በ30 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቃቸው ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን አስታውቀዋል።
በዛሬው ዕለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሚቴው ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ክልላዊ ፅህፈት ቤቱን ጥያቄ የሚቀበለው ከሆነ የሰው ኃይል አመዳደቡም ሆነ አፈፃፀሙ ይህ አደራጅ ኮሚቴና ጠቅላይ ቤተ ክህነት በጋራ የሚወስኑት እንደሚሆን ተገልጿል።
በተጠየቀው መሰረት አስቸኳይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ የምዕመኑን ጥያቄ ለመመለስ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚቴው አስጠንቅቋል። እርምጃው ምን እንደሆነ በዚህ ወቅት ግልፅ ባያደርጉም ከዚህ ቀደም እንደተናገሩት በራሳቸው ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት እናቋቁማለን ማለታቸው የሚታወስ ነው።
ቀሲስ በላይ በዚህ ወቅት እንደገለፁት ጉባኤው እምነቱ አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አንድ ፓትርያርክና አንዲት ቤተ ክርስቲያን መሆኑን አምነው የቤተ ክርስቲያኗን ሌላ ህግ ማውጣት እንደማያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት የማቋቋም ጥያቄ የቤተ ክርስቲያኗ የዶግማና የቀኖና ትውፊት ለውጥ ሳይኖር አስተዳደራዊ ችግሮችን ለመፍታት መዋቅር የማበጀት ጥያቄ መሆኑንም ገልፀዋል።
ጥያቄው አዲስ እንዳልሆነና ታሪካዊ ዳራ ያለው መሆኑን ተናግረው ቤተክርስቲያኗ በአፄ ኃይለ ስላሴ አገዛዝም ወቅት በጠቅላይ ግዛት በአውራጃና በወረዳ ደረጃ የመንግሥት አደረጃጀት ተከትላ ትሰራ እንደነበርና እንዲሁም በደርግ ወቅትም ይህ አሰራር እንደቀጠለ ገልፀዋል።
በኢህአዴግ አገዛዝም ወቅት የፌደራል አደረጃጀቱን ተከትሎ ኃገረ ስብከቶች መቋማቸውንና በክልል ደረጃ ፅህፈት ቤት

Share this post

One thought on “በሰላሳ ቀናት ውስጥ ሲኖዶስ መልስ ካልሰጠን አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን ሲል የኦሮሚያ ቤተክህነት ገለጸ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.