በሰሜን ወሎ ዞን በተከሰተው የበርሃ አምበጣ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረግ ድጋፍ ህጋዊ የመንግስት አሰራርን ተከትሎ እንደሚካሄድ የዞን አስተዳደሩ አስታውቋል፤ግለሰቦች የድጋፍ ሒሳብ ደብተር በመክፈት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ህጋዊነት እንደሌለውም ተጠቁሟል፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) ካለፈው መስከረም ወር መጀመሪያ ጀምሮ በሰሜን ወሎ ዞን የተከሰተው የበርሃ አምበጣ መንጋ በሰብል ላይ የከፋ ጉዳት አድርሷል፤ በተለይም በዞኑ ቆላማ አካባቢዎች የደረሰው ጉዳት በአርሶ አደሩ የምርት ሽግግር ወቅት የተፈጠረ መሆኑ ፈታኝ አድርጎታል ተብሏል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረትም በዞኑ ከ286 ሺኅ በላይ አርሶ አደሮች አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም ይታመናል፡፡ በሰሜን ወሎ […]

Source: Link to the Post

Leave a Reply