በስልጤ ዞን ከባድ ዝናብ ያደረሰው ጎርፍ የሰው ሕይወት ቀጠፈ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/111560

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መስተዳደር  ስልጤ ወረዳ  የወረደው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ።
Image result for heavy rain in ethiopiaጎርፉ በአካባቢው በሚኖረው ኅብረተሰብ ላይ ያስከተለውን ጉዳት ለመጎብኘት በስፍራው የተገኙት የደቡብ ክልል የቀይ መስቀል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፦ አቶ ተሾመ ተክሌ በተለይ ለዶይቼ ቬለ (DW) እንደገለፁት በተፈጥሮ አደጋው የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።
ጎርፉ ከኅብረተሰቡ አቅም በላይ መሆኑንም ተናግረዋል። «ትናንት ስልጤ ዞን ላይ ከፍተኛ ዝናብ እና ጎርፍ ነበር። ሰው ተፈናቅሏል፤ የሦስት ሰው ሕይወትም አልፏል። ከባድ ዝናብ ነው የጣለው። ከኅብረተሰቡ የመቋቋም አቅም በላይ የኾነ ጎርፍ ነው። ጎርፉ [ሰዎችን] አፈናቅሏል፤ ቤቶችን ከነሥር መሰረታቸው መንግሏል።
ከአንድ ቤተሰብ ሦስት ሰው ይዞ ሄዷል። በርካታ ሰዎችን አፈናቅሏል። መስክ ላይ እያየን ነው ያለነው።»

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.