በስደት ላይ ሆነው ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚገልጽ ሰነድ ላልነበራቸው ዜጎች ፓስፖርት እየተሰጠ ነው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/74416

በስደት ላይ ሆነው ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚገልጽ ሰነድ ላልነበራቸው ዜጎች ፓስፖርት እየተሰጠ ነው

በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ተሰደው ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያሳይ ሰነድ ስላልነበራቸው ”አገር አልባ” ሆነው የቆዩ ዜጎች ፓስፖርት እየተሰጣቸው ነው ተባለ።
በተለያየ ምክንያት መኖሪያቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ የተለያዩ አገራት ዜጎች ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ እንደተሰጣቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
የሚኒስቴሩ ቃለ አቀባይ አቶ መለስ አለም በዛሬ መግለጫቸው እንዳሉት በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅና ወደ እነሱም የቀረበ የቆስላ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር የተሳካ ስራ እየተሰራ ነው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.