በሶማሊያ ሞቃዲሾ በደረሰ የሽብር ጥቃት በርካቶች መሞታቸው ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2012 በሶማሊያ ሞቃዲሾ በደረሰ የሽብር ጥቃት በርካቶች መሞታቸው ተነገረ፡፡ በሞቃዲሺ በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት በደረሰ የቦንብ ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ 3 ሰዎች ህይወታቸው ወዲያው ሲያልፍ 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ ተናግሯል፡፡

የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ሙክታር እንደገለጹት ጥቃቱን ያደረሰው አጥፍቶ ጠፊ ሞቃዲሾ ብሄራዊ ቲያትር ቤት አጠገብ ወደሚገኘው ሬስቶራንት በመግባት የያዘውን ቦንብ ራሱ ላይ አፈንድቷል፡፡የአጥፍቶ ጠፊው ጥቃት በዋናነት ያነጣጠረው ንጹኃን ሰዎች ላይ መሆኑንም የቃል አቀባዩ መረጃ ያስረዳል፡፡

በጥቃቱ ህጻናትን ጨምሮ ሌሎች ንጹኃን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን በስፍራዉ ላይ የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡  እስከ አሁን ድረስ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል አለመኖሩም ነው የተገለፀው፡፡የአልቃይዳ ክንፍ የሆነው አልሸባብ በተደጋጋሚ ሞቃዲሾ ላይ የሽብር ጥቃቶችን ሲያደርስ መቆየቱን አስታውሶ አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply