በሸካ ዞን ተቃውሞው ቀጥሏል

Source: https://mereja.com/amharic/v2/42852

በሸካ ዞን ተቃውሞው ቀጥሏል
(በውብሸት ታዬ)
-ሆቴሎችና ባንኮች ተዘግተዋል
-የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል
-ተቃውሞው አራተኛ ቀኑን ይዟል

ከሁለት ሳምንት በፊት አንድ የ’መንጃ’ ብሔረሰብ አባል በአንድ ከፊቾ(የከፋ ብሔረሰብ አባል) ላይ ግድያ ፈጽሟል በሚል መነሻ በተቀሰቀሰ ግጭትና የበቀል እንቅስቃሴ በርካታ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን በሰው አካል ላይም ጉዳት መድረሱን በቦታው የተገኘው ባልደረባችን ዘግቧል።

የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከሳምንት በፊት የተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል በየኪ ወረዳ ቴፒ ከተማ በመገኘት በከተማው አዳራሽ የማሕበረሰቡን ተወካዮች ያነጋገሩ ሲሆን፤ በውይይቱ ወቅት የተወሰኑ አካላት ተደራጅተው ወደአዳራሹ በመሄድና እየደረሰብን ነው ያሉትን ጥቃት በተቃውሞ በሚገልጹበት ወቅት የተጠቀሙባቸው ቃላት የአከባቢውን ቀደምት ማሕበረሰቦች ክብር የሚነካ በመሆኑ ለችግሩ እዚህ መድረስ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.