በቀለ ገርባን ጨምሮ አራት የኦፌኮ አመራሮች ለ2ኛ ጊዜ ተፈረደባቸው

Source: http://ethioforum.org/amharic/%E1%89%A0%E1%89%80%E1%88%88-%E1%8C%88%E1%88%AD%E1%89%A3%E1%8A%95-%E1%8C%A8%E1%88%9D%E1%88%AE-%E1%8A%A0%E1%88%AB%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8A%A6%E1%8D%8C%E1%8A%AE-%E1%8A%A0%E1%88%98%E1%88%AB%E1%88%AE/

“ጠበቆች ከተነሱ ተከሳሾች እንዲነሱ አይገደዱም” ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴን (በጌታቸው ሺፈራው) የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር በቀለ ገርባን ጨምሮ አራት የድርጅቱ አመራሮች በድጋሜ በችሎት መድፈር ተፈረደባቸው። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ…

Share this post

One thought on “በቀለ ገርባን ጨምሮ አራት የኦፌኮ አመራሮች ለ2ኛ ጊዜ ተፈረደባቸው

 1. …. ተከሳሾቹ “ባለፈው በመናገራችን ተቀጥተናል” በሚል አንነሳም ማለታቸውን በጠበቆች በኩል ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል። ተከሳሾቹ ስማቸው በሚጠራበት ወቅት ባይነሱም እጃቸውን ያወጡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ካልተነሱ የፍርድ ቤቱን ሕግ ስላላከበሩ እርምጃ እንወስዳለን ብሏል።

  የተከሳሾቹ ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴን በበኩላቸው በፍርድ ቤት ማንነትን ማረጋገጥ የሚያስፈልገው ክስ ሲነበብ እንደሆነ፣ መዝገቡ ለዛሬ ጥር 28/2010 የተቀጠረው ለክስ መስማት (ማንበብ) ሳይሆን ፍርድ ለመስጠት ስለሆነ ጠበቆቹ ከቆሙ ተከሳሾች እንዲነሱ አይገደዱም ብለዋል።

  ሆኖም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ባለመቆማቸው ምክንያት የፍርድ ቤቱ ሰዓት በ30 ደቂቃ እንደባከኑና ድርጊቱንም ችሎት መድፈር መሆኑን በመግለፅ ውሳኔውን አስተላልፏል። ተከሳሾቹ ጥር 10/2010 በነበረው ቀጠሮውም በችሎት መድፈር በ6 ወር እስር መቀጣታቸውን አስታውሶ፣ ከባለፈው አልተማሩም በሚል ለ2ኛ ጊዜ የ6 ወር እስር ቅጣት ወስኗል። ጥር 10/2010 ዓም ችሎት ደፍራችኋል በተባሉበት ወቅት በፍርድ ቤት የተናገሩት ተከሳሾቹ ስለዛሬው ውሳኔው አልተናገሩም።
  *************************
  ++ ፍርድ ቤቱ መቅጣት የነበረበት ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴን ነበር።(የአዋቂ አጥፊ) ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ፍርድ ቤት የተሰማ ታሪክ መሆን አለበት። ተከሳሾች በሕመም ወይም ጽኑ የመንቀሳቀስ ችግር ኖሮባቸው በአልጋ ካልቀረቡ በቀር እጅ ማውጣት ከሁለተኛ ደረጃ በታች ላሉ ተማሪዎች ሥም ሲጠራ፡ ለእድርና እቁብ ላይ ብቻ ነው። ቢሆን ለሚጠራው ክብር ሲባል ተጠሪው ተነስቶ ባርኔጣ ቢያደርግ ያወልቃል።
  ******አዳሜ እራሱንም ሀገርና ሥራዓት እያቀለለና እየዘረጠጠ ወያኔ አጠፋን እያለ እጁን ይቀስራል ልበል!?***
  እኔ የምለው ለነጻነትና ዕኩልነት ለሕግ የበላይነት ሲታገሉ የታሰሩ ሰዎች ሥልጣን ቢይዙ ምን ዓይነት የሕግ ሥርዓት ሊመሰርቱ ነው? በእስካፒና ፕላስማ እቤት ቡና እየተጠጣ፡ ጫት እየተቃመ፡ የሚሠራ ዲሞክራሲያዊ መንግስትና ሕግ ሚ/ር ሊመሠርቱ ነው? ባለፈው ዘምረው እንጂ ቆመው ተሟግተው አልነበረም የተቀጡት፡ ዛሬ ግን ተናግረው ቢቀጡ ይሻል ነበር ተቀምጠው ከሚታሰሩ። ይቺ አወኩሽ ናኩሽ ያስተዛዝብ እንደሁ እንጂ አያስተዛዝንም።ትልቅ ስሕተት!!

  Reply

Post Comment