በቀላሉ እንዳይከፈት በኮንቴይነር ታሽጎ ወደ ውጭ ከተላከ ቡና ላይ በረቀቀ መንገድ ተከፍቶ ስርቆት የተፈጸመባቸው ላኪዎች ተበራክተዋል፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75421

Reporter Amharic

እስካሁን ከ150 ኩንታል በላይ የተሰረቁ እንዳሉ ታውቋል
በቀላሉ እንዳይከፈት በኮንቴይነር ታሽጎ ወደ ውጭ ከተላከ ቡና ላይ በረቀቀ መንገድ ተከፍቶ ስርቆት የተፈጸመባቸው ላኪዎች ተበራክተዋል፡፡ እስካሁን ስድስት ላኪዎች የሥርቆቱ ሰለባ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ሪፖርተር ባደረገው ማጣራት ቴስቲ ኮፊ፣ ሙለጌ፣ አባሃዋ ኩባንያ፣ ሲዳማ ቡና አምራቾች ኅብረት ሥራ ዩኒየን፣ ፋህም ጄኔራል ትሬዲንግና ሌሎችም ወደ ውጭ በኮንቴይነር አሽገው የላኩት ቡና በረቀቀ መንገድ ጎድሏል፡፡
የቴስቲ ኮፊ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፈይሰል አብዶሽ ዮኒስ፣ ወደ ኮሪያና አውስትራሊያ ከላኩት ቡና ላይ በጠቅላላው 31 ኩንታል እንደጎደለባቸው ተናግረዋል፡፡ ይኸውም በኮሪያ ቡሳን ከተማ ለሚገኘው ደንበኛው ከላኩት አንድ ኮንቴይነር (210 ኩንታል) ቡና ውስጥ 15 ኩንታል ሲወሰድ፣ ወደ ሲድኒ ከላኩት ውስጥ ደግሞ 16 ኩንታል ጎድሎ መገኘቱን ገዥው እንዳሳወቃቸው ገልጸዋል፡፡
የሲዳማ ቡና አምራቾች ኅብረት ሥራ ዩኒየን በበኩሉ ወደ ጀርመን ከላከው 210 ኩንታል ቡና ውስጥ 53.6 ኩንታል እንደጎደለ አስታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ወደ ጃፓን ዮኮሐማ ከተማ ለሚስቱቢሺ ከተላከ ቡና ውስጥ 30 ኬሻ፣ አንዳንዶቹም 100 ኬሻ ወይም 60 ኩንታል የጎደለባቸው እንዳሉ ተሰምቷል፡፡ ፋህም የተሰኘው ላኪ ኩባንያ በትንሹ የ8.4 ኩንታል ቡና ጉድለት እንዳጋጠመው ታውቋል፡፡
እነዚህ መረጃዎች ከዚህም ከዚያም የተገኙ እንጂ በተደራጀ መንገድ የተገኙ ባለመሆናቸው የችግሩ መጠንና ስፋት ምን ያህል እንደሆነ በሚገባ እንደማያሳይ ይታወቃል፡፡ በዚህ ደረጃ እንኳ የተደረሰበት ጉድለትና የተፈጸመው ስርቆት ወይም ቅሸባ በትንሹ በ150 ኩንታል ቡና ቢገመት እንኳ፣ ከ64 ሺሕ ዶላር በላይ ወይም በ28 ብር ገደማ ምንዛሪ ሲተመን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.