በትራንስፖርት ሚኒስቴር እና በቤልጅየም የትራንስፖርት ምርምር ማዕከል መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%89%A0%E1%89%B5%E1%88%AB%E1%8A%95%E1%88%B5%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B4%E1%88%AD-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%89%A0%E1%89%A4%E1%88%8D%E1%8C%85%E1%8B%A8%E1%88%9D/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና በቤልጅየም የትራንስፖርት ምርምር ማዕከል ሀስሌት ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት በኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ህይወት ሞሲሳ ናቸዉ፡፡

ስምምነቱ በዋናነት የመንገድ ደህንነት ሥራዎችን በኢትዮጵያ ከማሻሻል አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረዉ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም በአቅም ግንባታም ረገድ የትምህርትና የልምድ ልዉዉጥ ማድረግ የስምምነቱ አካል ሲሆን የተለያዩ ሲምፖዚያሞችና ወርክሾፖችን በማድረግ የዕውቀት ሽግግር የሚደረግበት በመሆኑ የትራንስፖርት ዘርፉን ዉጤታማነት ለማሻሻል ያግዛል ተብሏል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ 11 ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ከትራንስፖርት ጋር ተያያዥነት ያለዉ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸዉ በመማር ላይ እንደሚገኙ የገለጸው የትራንስፖርት ሚኒስቴር ነው፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.