በነሐሴ የመጀመሪያ አጋማሽ ቀናት ከ256 ሺህ በላይ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉ ተገለጸ

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በተያዘው ወር እየተካሄደ ባለው የማኅበረሰብ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በ15 ቀናት ከ256 ሺህ በላይ ሰዎች ምርመራ እንደተደረገላቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ÷ በዚህ ወር የተጀመረው የማኅበረሰብ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። በዘመቻው የአፍና አፍንጫ መሸፈን መርሃ ግብር /ማስክ ኢትዮጵያ/ መጠናከሩን ገልጸው ክልሎችም መርሃ ግብሩን በራሳቸው መንገድ እየሰሩበት መሆኑን ጠቁመዋል። ለአብነትም ሀረሪ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ግንባር ቀደም መሆናቸውን ጠቁመው ሌሎችም ተመሳሳይ ሂደት ላይ ናቸው ብለዋል። ዘመቻው በተለያዩ የመገናኛ ስልቶች እንዲሁም ቤት ለቤት በመሄድ በማስተዋወቅ ኅብረተሰቡ በዘመቻው ተሳታፊ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ጎን ለጎንም በተለይ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ

The post በነሐሴ የመጀመሪያ አጋማሽ ቀናት ከ256 ሺህ በላይ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉ ተገለጸ appeared first on ዘ-ሐበሻ Ethiopian Latest News & Point of View 24/7.

Source: Link to the Post

Leave a Reply