በነገው ዕለት የእስልምና እምነት ተከታዮች ሰልፍ እንዲያካሂዱ የተጠራው ሰልፍ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት እውቅና ውጪ ነው ተባለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/189101

በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ነገ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሰልፍ እንዲያካሂዱ የተጠራው ሰልፍ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እውቅና ውጪ መሆኑ ተገልጿል።
የምክር ቤቱ ጸሀፊ ሀጂ ሼህ ቃሲም ታጁዲን ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፥ ሰሞኑን በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ የተከሰተውን አደጋ ተከትሎ ተጠራ የተባለው ሰልፍ ከምክር ቤቱ እውቅና ውጪ መሆኑን አስታውቀዋል።
ስለሆነም ህዝበ ሙስሊሙ በነገው ዕለት የሶላት ስነ ስርዓቱን እንደ ከዚህ ቀደሙ በተረጋጋ መልኩ እንዲያከናውን አሳስበዋል።
ምዕመናን የእስልምናን አስተምህሮ በመተግበር ለዘመናት የዘለቀውን የመቻቻል ባህል ሊጠበቁ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የሁሉም ሀይማኖትተከታዮች መሰል ጥፋቶችን በማውገዝ ጥፋትን በጥፍት ለመክፈል የሚስተዋለውን ሁኔት በቅንጅት ማስወገድ እንደሚገባቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.